1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬደዋ የጸጥታ ይዞታና የምርጫ ዝግጅት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 20 2013

በድሬደዋ አስካሁን ካለው የምርጫ ሂደት ጋር በተያያዘ በምርጫ አስፈፃሚዎች ላይ የተፈፀመ መጠነኛ ድብደባን ጨምሮ አራት ወንጀሎች ማጋጠማቸውን የመስተዳድሩ ፖሊስ ገለፀ፡፡

https://p.dw.com/p/3shJJ
Äthiopien | Polizeikommission in Dire Dawa | Alemu Merga
ምስል Mesay Mekonnen/DW

«ፖሊስ ክትትል እያደረገ ነው»

በድሬደዋ አስካሁን ካለው የምርጫ ሂደት ጋር በተያያዘ በምርጫ አስፈፃሚዎች ላይ የተፈፀመ መጠነኛ ድብደባን ጨምሮ አራት ወንጀሎች ማጋጠማቸውን የመስተዳድሩ ፖሊስ ገለፀ፡፡ በመስተዳድሩ ከሚወዳደሩ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የፖሊስ ሥራ የሚመሰገን ነው ብሏል። ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ «ሰዎች ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይሄዱት የሚያስፈራራቸው አካል አለ የሚል ጥርጣሬ ነበረን» ያሉት የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር አለሙ መግራ ማንነቱን ባይገልጡም በተሰራ የፀጥታ ሥራ የተሻለ ውጤት መገኘቱን አመልተዋል። በመስተዳድሩ ከሚወዳደሩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/ አብን ድሬደዋ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ የሺጥላ ማሞ የፀጥታው ሁኔታ ጥሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ያለው የፀጥታ ማስከበር ስራ ጥሩ ቢሆንም ህብረተሰቡ ውስጥ ስጋቶች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

መሣይ ተክሉ 

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ