1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና የገጠሟቸው ሳንኮች፣

ማክሰኞ፣ ኅዳር 28 2003

በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር እንደአስፈላጊነቱ እንዲጨምር መደረጉ ትክክለኛና ማለፊያ ተግባር መሆኑን ማንም አይስተውም።

https://p.dw.com/p/QRr6
ምስል AP GraphicsBank/DW

እርግጥ ነው ፣ ትምህርት ተቋም ከመገንባት በፊት ፣ ቅድመ ጥናት ማካሄድ፣ ለተቋማት ፤ ለተማሪዎች የሚያስፈልጉትን አሟልቶ ማቅረብ ግድ ይላል። ለምሳሌ ያህል በቅርቡ በአንድ ዘገባችን ላይ እንዳወሳነው፣ የአክሱም ዩኒቨርስቲ አንዳንድ የመጽሐፍት መደርደሪያዎቹ፣ ባዶ በመሆናቸው፣ ከዴንቨር፣ ኮላራዶ ፣ ዩናይትድ እስቴትስ በበጎ አድራጎት 9 ቶን መጽሐፍት ተሰብስቦ ተልኳል።

በምሥራቃዊው ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች፣ በከፍሎች መጨናነቅ፣ በቦታ ርቀት፣ በውሃ እጥረትና በትኋን ጭምር እንደሚቸገሩ የሰማው ዘጋቢአችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ስለ ስለመፍትኄው ጭምር ኀላፊዎችን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልሠመረለትም። የተማሪዎቹን ችግር ግን እንደሚከተለው አቅርቦታል።

አበበ ፈለቀ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ