1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬዳዋ ፖሊስ ሥልጠና

ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2011

የከተማይቱ ፖሊስ ኮሚሽን እንደሚለዉ «ተሐድሶ» የተባለዉ ሥልጠና በፖሊሶች ሥራ፣አሰራርና ሥርዓት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለማቃለል ይረዳል።ሥልጠናዉ ከአንድ ወር እስከ አንድ ወር ተኩል ይፈጃል ነዉ የተባለዉ

https://p.dw.com/p/3HWDm
Stadt Dire Dawa in Äthiopien
ምስል Hailegzi Mehari

የድሬዳዋ ፖሊስ ሥልጠና

 
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በከተማይቱ የሚገኙ ፖሊሶችን በሙሉ ዳግም ሊያሰለጥን ማቀዱን አስታወቀ።የመስተዳድሩ ፖሊስ አባላት ኃላፊነታቸዉን በአግባቡ አይወጡም የሚል ወቀሳና ትችት በተደጋጋሚ ይሰነዘርባቸዋል።የከተማይቱ ፖሊስ ኮሚሽን እንደሚለዉ «ተሐድሶ» የተባለዉ ሥልጠና በፖሊሶች ሥራ፣አሰራርና ሥርዓት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለማቃለል ይረዳል።ሥልጠናዉ ከአንድ ወር እስከ አንድ ወር ተኩል ይፈጃል ነዉ የተባለዉ።ሥልጠናዉ የሚጀመርበት ጊዜና ሥፍራ ግን በግልፅ አልተነገረም።

 መሳይ ተክሉ 

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋለም ወልደየስ