የድስልዶርፉ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ
ሐሙስ፣ ግንቦት 11 2003ማስታወቂያ
ዘንድሮ ጀርመን 56 ኛዉን የአዉሮጻ አገራት የሙዚቃ ዉድድር Eurovision Song contest ን አዘጋጅታ፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ አዘርባጃን አሸናፊ ሆናለች። ጀርመን በዉድድሩ አስረኛ ብትወጣም ዉጤቱን በደስታ ተቀብላ እንግዶችዋን አስተናግዳ ወደ መጡበት ሸኝታለች። በድስልዶርፍ ከተማ የሚገኘዉ ግዙፍ የእግር ኳስ ስቴድዮም በልዮ የኤሌክትሮኒክስ ዉጤት ወደ ትልቅ አዳራሽ ተቀይሮ ከምንግዜዉም በላይ የተዋጣለት መድረክ አዘጋጅቶም ነበር። አዳራሹን እንደገና ወደ ነበረበት የእግር ኳስ ሜዳ ለማድረግ የአንድ ሳምንት የስራ ግዜን እንደሚወስድ ተገልጾአል። የለቱ የባህል መድረካችን ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ እዚህ በድስልዶርፍ ከተማ የተካሄደዉን የሙዚቃ ዉድድር ያስቃኛል፣
አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ