1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዶናልድ ትራምፕ

ዓርብ፣ ሐምሌ 15 2008

ትራፕም 75 ደቂቃ በወሰደው ንግግራቸው የአሜሪካንን ደህንነት እንደገና ለማስጠበቅ ፣ ወደ አሜሪካ የሚደረግ ህገ ወጥ ስደትን ለማስቆም እና አሜሪካንን ታላቅ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ።

https://p.dw.com/p/1JUkV
ምስል Reuters/M. Segar

[No title]

41ኛው የአሜሪካን የሪፐብሊካን ፓርቲ ጉባኤ፣ ፓርቲውን ወክለው በእጩ ፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ የመረጣቸው ዶናልድ ትራምፕ ትናንት በፓርቲያቸው ጉባኤ ላይ ባሰሙት ንግግር፣ ሃገሪቷ የምትዋዥቅባቸውን ልዩ ልዩ ችግሮች ብቻቸውን ማስወገድ እንደሚችሉ አስታወቁ ። ትራፕም በእጩነት ከተሰየሙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባሰሙት 75 ደቂቃ በወሰደ ንግግራቸው የአሜሪካንን ደህንነት እንደገና ለማስጠበቅ ፣ ወደ አሜሪካ የሚደረግ ህገ ወጥ ስደትን ለማስቆም እና አሜሪካንን ታላቅ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ። አወዛጋቢው የ70 ዓመቱ ባለፀጋ ትራምፕ የኢንድያና ክፍለ ግዛት ሀገረ ገዥ ማይክ ፔንሰንን በምክትል እጩ ፕሬዝዳንትነት መርጠዋል ። የ45 ተኛው የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ ተፎካካሪ ምርጫ ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችም ተገኝተዋል ። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር አለው ።

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ