1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶናልድ ትራምፕ ጸያፍ ንግግርና የአፍሪቃ ኅብረት

ዓርብ፣ ጥር 4 2010

ወደ የዩናይትድ ስቴትስ የሚገቡ የውጭ ዜጎችን በሚመለከተው ሕግ ላይ በተደረገ ምክክር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገራቸው የሚገኙትን የአፍሪቃ እና ሐይቲ መጤዎችን የሚያንቋሸሽ ጸያፍ ንግግር ተጠቅመዋል።

https://p.dw.com/p/2qmNI
African Union Hauptquartier in Addis Abeba
ምስል AFP/Getty Images/J. Vaughan

የአፍሪቃ ኅብረት ምላሽ በዶናልድ ትረምፕ ጸያፍ ንግግር

ወደ የዩናይትድ ስቴትስ የሚገቡ የውጭ ዜጎችን በሚመለከተው ሕግ ላይ በተደረገ ምክክር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገራቸው የሚገኙትን የአፍሪቃ እና ሐይቲ መጤዎችን የሚያንቋሸሽ ጸያፍ ንግግር ተጠቅመዋል። የሀገሪቱ ጋዜጦች እንደዘገቡት ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ለምን ብላ ነው «ከነዚህ እጅግ ቁሻሻ ሃገራት» መጤዎችን የምትቀበለው ሲሉ ተደምጠዋል። የፕሬዚዳንቱ ጸያፍ ንግግር ከዩናይትድ ስቴትስ አንስቶ በመላው ዓለም ቁጣን ቀስቅሷል። ይኽን ጸያፍ ንግግር የአፍሪቃ ኅብረት እንዴት ይመለከተዋል በሚል የኅብረቱን  ቃል አቀባይ ወይዘሮ ኤባ ካሎንዶ ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ