1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶናልድ ያያማሞቶ የኢትዮጵያ ጉብኝት 

ዓርብ፣ ሚያዝያ 19 2010

የዩናይትድ ስቴትሱ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ በአፍሪቃ ቀንድ ሃገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት እንደቀጠሉ ነዉ። ዶናልድ ያማማቶ በመግለጫቸዉ ይበልጡኑ በሁለቱ ሃገራት መካከል ባለዉ ግንኙነት ላይ ማተኮራቸዉ ተገልፆአል።

https://p.dw.com/p/2woNK
Äthiopien Addis Abeba Donald Yamamoto
ምስል DW/G. Tedla

Ber. A.A (Jamamatos Äthiopien Besuch) - MP3-Stereo

 

የዩናይትድ ስቴትሱ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ በአፍሪቃ ቀንድ ሃገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት እንደቀጠሉ ነዉ። ከኤርትራ ቆይታቸው በኋላ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አዲስ አበባ የገቡት የዩናይትድ ስቴትሱ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ከማግኘታቸዉ ጥቂት ቀደም ሲል በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ከተገናኙ በኋላ አጭር መግለጫ ሰጥተዋል። ዶናልድ ያማማቶ በመግለጫቸዉ ይበልጡኑ በሁለቱ ሃገራት መካከል ባለዉ ግንኙነት ላይ ማተኮራቸዉ ተገልፆአል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባዉን አዘጋጅቶአል።   

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ