የዶክተር መረራ ክስ
ዓርብ፣ የካቲት 24 2009ማስታወቂያ
ዛሬ ያስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ነኛ ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ በኦሮሞ ፌደራላስት ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ላይ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ አዳምጧል ። አቃቤ ህግ ዶክተር መረራን አብሮ ከከሰሳቸው ከዶክተር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀ መንበር፣ ከአቶ ጅዋር ሞሀመድ የፖለቲካ እና የመብት ተሟጋች ፣የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት እና የኦሮሞ ሚድያ ኔትወርክ ጋር በጋራ እንዲሁም በግል አጥፍተዋል ያላቸውን አቅርቧል ። ችሎቱ ዶክተር መረራ ለክሱ በጠበቆቻቸው በኩል የሚያቀርቡትን የመቃወሚያ ሀሳብ ለመስማት እና ባቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ለመጋቢት 29፣2009 ዓምተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ