1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 ዶክተር አብይ በሳዑዲ አረብያ 

ዓርብ፣ ግንቦት 10 2010

ዶክተር አብይ በጅዲ ቆይታቸው ከተደረገለት ቀዶ ህክምና በኋላ ፣በሐኪሞች ስህተት ሳይነቃ ፣ላለፉት 13 ዓመታት ጂዳ ሆስፒታል የሚገኘውን ታዳጊ ወጣት መሐመድ አብዱልአዚዝን ዛሬ እንደጎበኙም በስፍራው የተገኘው  የጂዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ነግሮናል።

https://p.dw.com/p/2xxtC
Äthiopien Addis Abeba -  Äthiopiens Premierminister Dr Abiy Ahmed in Jeddah Karnkenhaus
ምስል DW/N. Sirak

ዶክተር አብይ በሳዑዲ አረብያ

ሳዑዲ አረብያን በመጎብኘት ላይ ያሉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ከሳዑዲ አረብያ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። ትናንት ማምሻውን ጂዳ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአልጋ ወራሹ ጋር ባደረጉት ዉይይት ካነሷቸዉ ፤ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የታሰሩ ኢትዮጵውያን እንዲፈቱ ያቀረቡት ጥያቄ አንዱ ነዉ። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያውያን እሥረኞችን ለመፍታት መወሰኑም ተገልጿል። ዶክተር አብይ በጅዲ ቆይታቸው ከተደረገለት ቀዶ ህክምና በኋላ ፣በሐኪሞች ስህተት ሳይነቃ፣ ላለፉት 13 ዓመታት ጂዳ ሆስፒታል የሚገኘውን ታዳጊ ወጣት መሐመድ አብዱልአዚዝን ዛሬ እንደጎበኙም በስፍራው የተገኘው  የጂዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ነግሮናል። ስለ ዶክተር አብይ የሳዑዲ ጉብኝት ከነብዩ ሲራክ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማዳመጥ ይችላል።

ነብዩ ሲራክ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ