1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶክተር ዐቢይ የአንድ ዓመት አስተዳደር

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 2 2011

ድርጅቱ በ8 ርዕሶች ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት እና ሌሎች መሰል መብቶች እየተከበሩ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እና በድርጅቱ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ከፍተኛ ተመራማሪ ፌሊክስ ሆርን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተባባሰው ግጭት ምክንያት የለውጡ ቀጣይነት እንደሚያሳስብ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3GZXr
Menschenrechte Logo human rights watch

«መንግሥት ህግና ስርዓት ሊያስከብር ይገባል»HRW

 ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ልዩ ልዩ መብቶች እየተከበሩ ቢሆንም የለውጡ ቀጣይነት ግን እንደሚያሳስበው አስታወቀ።ድርጅቱ ካለፈው ሳምንት አንስቶ በ8 ርዕሶች በተከታታይ ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት እና ሌሎች መሰል መብቶች እየተከበሩ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እና በድርጅቱ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ከፍተኛ ተመራማሪ ፌሊክስ ሆርን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተባባሰው ግጭት ምክንያት የለውጡ ቀጣይነት እንደሚያሳስብ ተናግረዋል። መንግሥት ግልጽ እቅድ በማውጣትም ህግ እና ስርዓትን ሊያስከብር እንደሚገባም አሳስበዋል። ያነጋገራቸው ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ