1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 29 2009

ለዓለም የጤና ድርጅት መሪነት በእጩነት የቀረቡት የቀድሞ የጤና ጥበቃና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶከተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከሌሎች አምስት እጩዎች ጋር በመሆን ተቋሙን እንዴት መምራት እንደሚፈልጉ እና ግባቸውን ለአባል ሀገራት ተወካዮች አስረድተዋል።

https://p.dw.com/p/2SMHA
Deutschland Bonn Sitz der UN United Nations Institute for Environment and Human Security
ምስል picture-alliance/dpa/O. Berg

Dr. Tedros Candidacy for WHO - MP3-Stereo

በዚሁ መድረክ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል።ዶክተር ቴዎድሮስ ንግግራቸዉን ሲጀምሩ የዓለም የጤና ድርጅት አባል ሀገራት የገንዘብ መዋጮ በጣም አናሳ እንደሆነና ተቋሙ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ (Emergency Response)ላይ ወደ ኋላ መቅረቱን ይህን ለማሻሻልም እንደሚሰሩ ገልፀዋል። «አብረን ለጤናማ አለም » የሚል መርህ ይዘው የተነሱት ዶክተር ቴዎድሮስ የዓለም አቀፉ የጤና ተቋም «ጤና ለሁሉም» የሚለውን ግብ እዉን ለማድረግ ለምን አቃተዉ ብለውም ተችተዋል። 

«በ1947 የአለም ጤና ደርጅት በተቋቋመበት ግዜ ጤና ለሁሉም ብለን ነበር። በ1970 አልማታ ስምምነት ተመሳሳይ ነገር ነዉ ያልነዉ። በ2016 ደግሞ ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን ወይም ጤና ለአለም  ነዉ እያለን ነዉ። ግን ለስድስት አስርተ ዓመታት ያልነውን ስራ ላይ እያዋልን አይደለንም። ጥያቄዉ የገቢ ምንጭ እጦት ነዉ? አይመስለኝም ብዙም ሰዉ አይሰማማበትም። ምክንያቱም ሀገራት በተወሰነ የገቢ ምንጭ እንኳን ተግባራዊ እያደረጉት ነው።» 

በንግግራቸዉም ደክተር ቴዎደሮስ ለዚህ ቦታ ብቁ የሚያደርጋቸው ምን እንደሆነ እንደሚጠየቁ  ጠቅሰው፣ ኢጩ ልሆን እችላለሁ ያሉበትን አራት ምክንያቶችን  ዘርዝረዋል፣ «አንድ ተነሳሽነት አለኝ። ሁለተኛ በአገር ዉስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ለዉጦችን ለማምጣት በቂ ልምድ አለኝ።ሦስተኛ የአለም የጤና ድርጅት የሚፈልጋቸዉን ቴክንካዊ ክህሎት ፣ ፖለቲካዊ አመራር  እና ዲፕሎማሲያዊ ችሎታ አለኝ ። አራተኛዉ እኔ ከታዳጊ አገር በመሆኔ በታዳጊ ሀገሮች ያሉትን የጤና ችግሮች  አውቃቻዋለሁ። ስለዚህ ወደ አለም የጤና ድርጅት አዲስ እይታ ማምጣት እንችላለን።»   

በዚህ ጉዳይ ላይ የህክምና ባለሙያው ዶክተር ቴዉድሮስን በቅርበት አዉቃዋለዉ የሚሉት እና አሁን የክልንተን ሄልዝ አክሰስ እንሼትቭ  የተባለው ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክቴር ዶክተር ይገርሙ አበበን አነጋግረን ነበር። እሳቸዉም ዶክተር ተዉድሮስን የማዉቀዉ በትግራይ ክልል የወባ መከላከል  ላይ አብረን ስንሰራ ነበር ይላሉ።

ይሁን እንጅ በጥያቄና መልሱ መድረክ ዶክተር ቴዎድሮስ ጠያቂዎቻቸውን ፣ጥያቄያቸዉ አልገባኝም በማለት እንድያብራሩላቸው በተደጋጋሚ መጠየቃቸዉ ፣ ዓለም አቀፉን ተቋም ለመምራት ያላቸዉን ብቃት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው ሲሉ የተቹትም ነበሩ።

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ