1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ቀብር ሥነ-ስርዓት ቀን በዉል አለመታወቁ ተገለፀ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2011

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ሥነ-ስርዓት መች እንደሚካሄድ ያረፉበት ሆስፒታል የመጨረሻ ምርመራ መረጃ እየተጠበቀ በመሆኑ ቀኑ በትክክል እንደማይታወቅ የተቋቋመው ብሄራዊ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ አደረገ፡፡

https://p.dw.com/p/3HiBN
Äthiopien Negaso Gidada
ምስል DW/Y.G. Egziabhare

ያረፉበት ሆስፒታል የመጨረሻ ምርመራዉን እስኪያጠናቅቅ እየተጠበቀ ነዉ

የቀድሞው የኢፌሬሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ሥነ-ስርአት መች እንደሚካሄድ ያረፉበት ሆስፒታል የመጨረሻ ምርመራ መረጃ እየተጠበቀ በመሆኑ ቀኑ በትክክል እንደማይታወቅ የተቋቋመው ብሄራዊ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ አደረገ፡፡ አስክሬናቸውም ወደ ሃገር በትክክል በዚህ ቀን ይመጣል ማለት ባይቻልም የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ላይ ሊሆን እንደሚችል ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጽዋል፡፡ የፕሬዝዳንቱ ህልፈት የተነገረበት መንገድ ህግን መሰረት ያደረገ ስለመሆኑም ኮሚቴው ህግ እንዳልተጣሰ ነገር ግን በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ፕሬዝዳንቷ ባህር ማዶ ስለነበሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ መገናኛዎች ይፋ አድርገውታል ብሏል ኮሚቴው፡፡ ህመማቸው ምን እንደነበርም አሁን ባለው ሁኔታ ሆስፒታሉ ሳያሳውቀን ይህ ነው ማለት አይቻልም ብሏል ኮሚቴው በመግለጫው፡፡ ስርአተ ቀብሩ ግን በክብር እንደሚከናወንና የተቋቀወመው ኮሚቴ ስራውን በትክክል እየሰራ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡

ሰለሞን ሙጬ


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ