1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶ/ር ዳኛቸው መታሰቢያ ነጻ የትምህርት ዕድል፣

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 27 2002

ኢትዮጵያ ፣ በ 5 ዓመት የአርበኞቿ ተጋድሎ፣ የወራሪውን የፋሺስት ኢጣልያን ጦር ድል በማድረግ ከስደት ከተመለሱት ንጉሠ-ነግሥትዋ ጋር ፣

https://p.dw.com/p/NFAR
ምስል AP

የተመለሰውን ነጻነትዋን ከ 69 ዓመት በፊት ማክበር የጀመረችበት የድል መታሰቢያ በዓል ነው። በዚያ ዘመን የነበሩት አርበኞችዋ ጊዜው የሚጠይቀውን ተጋድሎ በመፈጸም ላገራቸው ቤዛ መሆናቸውን በጽኑ ተግባራቸው አሥመሥክረዋል። የውጭ ወራሪን መክቶና ድል አድረጎም ማስወጣት አንዱ ጀግንነት ነው። ድኅነትን፣ ኋላ-ቀርነትን መፋለም ደግሞ ሌላው ጀግነነት ነው። እንደምሳሌም፣ እዚህ ላይ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ፣ ምርጥ እህል በሰፊው በማምረት አገሪቱ፣ ከድኅነት እንድትገላገልና ረሀብን እንድታስወግድ በሰፊው ይጥሩ የነበሩትን ትልቁን ኢትዮጵያዊ የአዝርእት ተመራማሪ ሳይንቲስት ዶ/ር ዳኛቸው ይርጉን ማስታወስ ይቻላል።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ