1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ጉብኝት

ማክሰኞ፣ ጥር 21 2011

ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ባለፈዉ እሁድ ምሽት አዲስ አበባ የደረሱት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ አዲስ አበባ የሚገኘዉን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲን ጎበኙ። የኢትዮጵያ እና የጀርመን ግንኙነት ለውጡን ወደ መደገፍ ትብብር ከፍ ማለቱን ፕሬዝዳንቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳዉቀዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/3CLwh
Äthiopien Bundespräsident Steinmeier besucht einen Berufskolleg in Addis Abeba
ምስል DW/A. Steffes
Äthiopien Bundespräsident Steinmeier besucht einen Berufskolleg in Addis Abeba
ምስል DW/A. Steffes

ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ባለፈዉ እሁድ ምሽት አዲስ አበባ የደረሱት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ አዲስ አበባ የሚገኘዉን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲን ጎበኙ። የኢትዮጵያ እና የጀርመን ግንኙነት ለውጡን ወደ መደገፍ ትብብር ከፍ ማለቱን የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ትናንት ከኢትዮጵያዋ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ አሳዉቀዉ ነበር።  ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ይህንኑ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩም ማረጋገጣቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በትዊተር ገጹ መዘገቡ ይታወቃል። ሽታይንማየርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩት ዶክተር ዐብይ «የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ ሲሰጥ የቆየውን እና አሁንም የቀጠለውን የቴክኒክ እና የሞያ ዘርፍ ድጋፍ ማድነቃቸው»ተገልጿል። ሽታይንማየር ከኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት የጋራ መግለጫ ላይ ጀርመን በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ መደገፍ እንደምትፈልግ ፣በኢትዮጵያ የሚካሄደው ለውጥም ለአፍሪቃም ሆነ ለአውሮጳ መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆኑን አስታውቀዋል። ሽታይንማየር በኢትዮጵያ የሚካሄደው ለውጥ የተቀረው ዓለም ስለአፍሪቃ ያለውን አመለካከት እንዲያስተካክል የሚያግዝም ነው ብለዋል። የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ወደ ኢትዮጵያ ከመጉዋዛጠዉ በፊት ከጋዜጠኞች በቀረበላቸዉ ጥያቄ ሲመልሱ «ጀርመን ከአዉሮጳ ጠንካራ ምጣኔ ሐብት ያላት በመሆንዋ ድጋፍ ማድረግ ከፈለገች ድጋፉ በፖለቲካዊ ትብብር አማካኝነት፣ በማማከርና ተቋማትን በመገንባት ሊደረግ ይችላል። ይሁንና ከዚሕም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ መንግሥታቸዉ፣ ባጠቃላይ ሐገሪቱ የምጣኔ ሐብት ማነቃቂያ ያሻታል። ለዚሕም ነዉ አሁን የምጓዘዉ ብቻዬን ሳይሆን ከኩባንያና ከንግድ ተቋማት ባለቤቶችና ኃላፊዎች ጋር የሚሆነዉ። ከእነዚህ መሐል ገሚሶቹ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ አዉቃለሁ።ይሕም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በጀመሩት እንዲቀጥሉ ይረዳቸዋል የሚል ተስፋ አለኝ።» ሲሉ ተናግረዉ ነበር

Äthiopien Bundespräsident Steinmeier besucht einen Berufskolleg in Addis Abeba
ምስል DW/A. Steffes
Äthiopien Frank-Walter Steinmeier zu Besuch in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Geberegziabher

አዜብ ታደሰ