1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሽታይንማየር የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎበኙ

ማክሰኞ፣ ጥር 21 2011

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎበኙ። ፕሬዚዳንቱ ወደ ላሊበላ ከማቅናታቸው በፊት በጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት ድጋፍ የሚደረግለትን የፌደራል ቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩትም ጎብኝተዋል።

https://p.dw.com/p/3COKX
Äthiopien Bundespräsident Steinmeier besucht Felsenkirche von Lalibela
ምስል Fana Broadcasting Corporate

ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ባለፈዉ እሁድ ምሽት አዲስ አበባ የደረሱት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎበኙ። ፕሬዚዳንቱ ወደ ላሊበላ ከማቅናታቸው በፊት በጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት ድጋፍ የሚደረግለትን የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩትም ጎብኝተዋል። በላሊበላ ቆይታቸውም ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ኾነው መልእክት አስተላልፈዋል። 

«ትናንት አዲስ አበባ ከፕሬዚዳንቷ፣ ከጠቅላይ ሚንሥትሩ፣ እንዲሁም በሀገሪቱ በሚታየው የፖለቲካ ለውጥ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከኾኑ በርካታ ሰዎች ጋር በፖለቲካ ንግግር የተሞላ ቀን ነበር። ዛሬ በኢትዮጵያ ታላቅ በዓል ነው። የማርያም እረፍት ቀን። እናም አጋጣሚውን በመጠቀም እዚህ ሰሜን ኢትዮጵያ መጥተናል። ከጠቅላላው የጀርመን ልዑካን ጋርም በዓለም ቅርስ የተመዘገበችውን ከተማ እየተመለከትን ነው።» 

ጎይተ ኢንስቲትዩትን እና የጀርመን የትምህርት እድልን ጨምሮ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ቆየት ያለ የባሕል ግንኙነት እንዳላት የጠቆሙት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት አሁን በኢትዮጵያ እየታያ ነው ያሉት ለውጥ በባሕልም የበለጠ ጥብቅ ትስስር ለመፍጠር እድል ከፋች ነው ብለዋል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

አዜብ ታደሰ