1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት 2ኛ ዘመነ ስልጣን ያለመፈለግ

ሰኞ፣ ግንቦት 29 2008

የጀርመኙ ፕሬዚዳንት ዮአኺም ጋውክ ዕድሜያቸዉ እየገፋ በመሄዱ ምክንያት የሁለተኛ የስልጣን ዘመን ሃላፊነትን መቀበል እንደማይችሉ ገለፁ።

https://p.dw.com/p/1J1Vi
Deutschland Joachim Gauck
ምስል Reuters/H. Hanschke

[No title]

ከጀርመን ምክር ቤት ተወካዮች መካከል 75 % ያህሉ ጋዉክ ስልጣኑን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ይፈልግ ነበር። 76 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ዮአኺም ጋዉክ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ግን ተጨማሪ አምስት ዓመት በስልጣን ቆይቼ በትክክል ስራዬን ለማስፈፀም እችላለሁ ብዬ ዛሬ መናገር አልችልም ሲሉ ነዉ ምክንያታቸዉን የገለፁት። ለአምስት ዓመታት የሚዘልቀዉ የጀርመን ፕሬዚደንትነት ሥልጣን ሃገሪቱን ወክሎ የተለያዩ ሥራዎችን ከማከናወንና፤ አባታዊ ተግሳፅና ምክርን ከመስጠት በቀር ፖለቲካዊ ዉሳኔዎች ላይ አይሳተፍም። ተወዳዳሪው የሚመረጠዉ ወይም በእጩነት የሚቀርበዉ በምክር ቤት በሚገኙ የተለያዩ ፖለቲካ እንደራሴዎች ነዉ። የፕሬዚዳንት ዮአኺም ጋውክ በስልጣን አለመቀጠል በሃገሪቱ ፖለቲካ እና በአዉሮጳ ፖለቲካ ላይ የሚያመጣዉ ተጽዕኖ ምን ይሆን?

አዜብ ታደሰ

ይልማ ኃይለሚካኤል

ኂሩት መለሰ