1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመናውያን ተቋማት ፀረ ሙስና ትግል

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 3 2010

የውጭ ተቋማት ገንዘባቸውን ሙስና በሚታይባቸው ሀገራት ውስጥ በሚያሰሩበት ጊዜ  ሁሌ ትክክለኛውን አሰራር አይከተሉም በሚል ይወቀሳሉ። በአፍሪቃ የሚንቀሳቀሱ የጀርመን ተቋማት እና አፍሪቃውያን መንግሥታት ይህን የተባለውን ሙስና ለማስወገድ ጥረት ጀምረዋል። 

https://p.dw.com/p/2vq07
Deutschland Logo von Softwarehersteller SAP in Walldorf
ምስል picture-alliance/dpa/U. Deck

በውጭ ኩባንያዎች ላይ የተሰነዘረው ወቀሳ

በደቡብ አፍሪቃ በሚንቀሳቀሰው የጀርመናውያኑ የሶፍትዌር ተቋም፣ ኤስ ኤ ፒ ላይ ሰሞኑን አዲስ ወቀሳ ተሰነዘረ። ተቋሙ ይህ ወቀሳ እንዳይሰነዘር ማስስወገድ ቢችል ኖሮ ደስ ባለው ነበር፣ ምክንያቱም፣ ከደቡብ አፍሪቃ የመንግ/ስት መ/ቤቶች እና ተቋሞች ጋር የሚያደርጋቸው የስራ ግንኙነት ይሳኩ ዘንድ ብዙ ገንዘብ ፣ ትክክል ባይሆንም፣ ይከፍላል በሚል ከብዙ ጊዜ w።ዲህ ወቀሳ እየቀረበበት ነው። አዲሱ ወቀሳ ኤስ ኤ ፒ ለደቡብ አፍሪቃ የውኃ ሚንስቴር ሶፍትዌር የመጠቀም ፈቃድ የሸጠበት ሁኔታ ትክክለኛውን መንገድ ያልተከተለ ነበር የሚል ሲሆን፣ የሀገሪቱ ፀረ ሙስና መስሪያ ቤት ተቋሙ ሕግን ማክበር አለማክበሩን በማጣራት ላይ ይገኛል። ኤስ ኤ ፒ ባለፈው መጋቢት መጀመሪያ ገደማ ባደረገው የውስጥ ምርመራ ስህተት መፈፀሙን በማስታወቅ፣ ከደቡብ አፍሪቃ ጋር ለመተባበር  ዝግጁነቱን ገልጿል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሙስናን እየመረመረ መዘርዝር የሚያወጣው ድርጅት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባልደረባ ኬት ምዌኪ ይህን የተቋሙን ርምጃ አበረታቺ ብለውታል። 
« ተቋሙ ትብብር አሳይቷል። ጥፋተኝነቱን የተቀበለው እና በምርመራው ለመተባበር ዝግጁ የሆነው፣ እንዲሁም፣ ኃላፊዎቹን ከስራ ለጊዜው ያገደው እና የሚሰጣቸውን ክፍያ ያቆመው ፈጥኖ ነበር። እና ይህ ኤስ ኤ ፒ ለቀረቡበት ወቀሳዎች ምላሽ በመስጠቱ ረገድ የወሰደው አንድ አዎንታዊ ምልክት ሆኖ ታይቷል። »
በኤስኤፒ ላይ የቀረበው ወቀሳ የውጭ ተቋማት ገንዘባቸውን ሊያሰሩባቸው የሚፈልጉ ሀገራት ሙስና የሚታይባቸው ከሆኑ ተቋማቱ ምን ማድረግ ይገባቸዋል በሚል ካሁን ቀደም የተሰማ ጥያቄ እንዳዲስ እንዲነሳ ምክንያት ሆኗል። ብዙ ጀርመናውያን ተቋማት ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ትክክለኛ የመሰላቸውን ሁሉ ማድረግ፣ ካስፈለገም ጉቦ መክፈል ድረስ መሄድ ተገቢ ነው የሚል አመለካከት ነበራቸው። ይህ አሰራራቸው ሙስናን እና ጨቋኝ መንግሥታትን ያበረታታል የሚለው አነጋገር ያን ያህል አያሳስባቸውም  ነበር። በውጭ ሀገር ተቋማት የሚፈጽሙት ጉቡ መክፈልን የመሰለ ድርጊት ጀርመን ሀገር ውስጥ  እስከ ሀያ ዓመት በፊት ድረስ አያስቀጣም ነበር።  እንዳውም ተቋማቱ በዚህ መንገድ የከፈሉትን ገንዘብ በሀገራቸው ከግብር ተመላሽ ማድረግ ይችሉ ነበር። መቅጫ ሕግ የወጣው በጎርጎሪዮሳዊው 2002 ዓም ነበር፣ ግን በዚህ ሕግ እስካሁን ክትትል ያረፈበት ተቋም የለም። 
ይህ ጉዳይ በመገናኛ ብዙኃን፣ በፖለቲከኞች እና በተቋማት ላዕላይ ቦርድ ውስጥ ትኩረት ያገኘው ትልቁ የጀርመን ተቋም፣ ዚመንስ በውጭ ሀገራት 1,3 ቢልዮን ዩሮ በአጠያያቂ መንገድ የከፈለበት ድርጊት ይፋ በወጣበት ጊዜ ነው። ዛሬ ዚመንስ ሙስናን ለማስወገድ በተጀመረው ትግል ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ከሚሳተፉት መካከል ይቆጠራል።  በጀርመን ኤኮኖሚ የአፍሪቃን ጉዳይ የሚያየው ማህበር ባልደረባ ክርስቶፍ ካንንጊሰር ለዶይቸ ቬለ እንዳሉት፣ ዚመንስ በዓለም አቀፍ ደረጃ 45o ሙስና ተቆጣጣሪ ሰራተኞች አሰማርቷል።
ሙስና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚንቀሳቀሱት ተቋማት  ይበልጥ ለራሱ ለአፍሪቃ ትልቅ ችግር ሆኗል። ይህ ለአህጉሩ በአስቸኳይ የሚያስፈልገውን ኢንቬስትመንት አንድም ያዘገያል ወይም ከነጭራuሼ ያስቀራል። በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል  መዘርዝር ውስጥ አብዛኞቹ አፍሪቃውያት ሀገራት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት።፣ ይሁንና፣ አፍሪቃ ለሙስና የተጋለጠ ነው ብሎ መፈረጅ እንደማይቻል ካንንጊሰር አመልክተዋል።
« አፍሪቃ ለየት ያለ አመለካከት ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ። ሙስና በአፍሪቃ ብቻ የሚታይ ክስተት አይደለም። 27 የአፍሪቃ ሀገራት፣ ማለትም፣ ከግማሽ የሚበልጡት በሙስና መዘርዝር ውስጥ የተሰጣቸው ። »
ባለፉት ጊዚያት በአህጉሩ የተካሄዱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫዎችም በምርጫ ዘመቻ ወቅት ሙስናን ለመታገል ቃል የገቡ የጋና ናኖ አኩፎ አዶን ወይም የላይቤሪያን ጆርጅ ቬይን የመሳሰሉ እጩዎች ማሸነፋቸው አህጉሩ ሙስናን ለመታገል ቆርጦ መነሳቱን የሚያሳይ ነው። በዚያም ሆነ በዚህ ግን የተገባ ቃል በተግባር ሲተረጎም ብቻ ነው ውጤታማ ሊኮን የሚቻለው።

Liberia George Weah als Präsident vereidigt
ምስል Reuters/T. Gouegnon
Nigeria Symbolbild Korruption
ምስል picture-alliance/AP Photo/S. Alamba
Südafrika Protest gegen Korruption ARCHIV
ምስል picture alliance/AP Photo/T. Hadebe

አርያም ተክሌ/ያን ፊሊፕ ቪልሄልም

ሂሩት መለሰ