1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመንን የምርጫ ዝግጅት የሚቃኘው የዶቼ ቬለ ጋዜጠኞች ጉዞ

ዓርብ፣ ነሐሴ 28 2013

ላለፊት 16 ዓመታት ሀገሪቱን በመራሂተ መንግሥትነት ያስተዳደሩት እና በዜጎቻቸው እናታችን በሚል ቁልምጫ የጀርመንኛውን ሙተር የሚል የእናት ትርጉም ሙቲ እያሉ የሚጠሯቸው አንጌላ ሜርክል የሥልጣን ዘመናቸው ማብቅያ ነው።

https://p.dw.com/p/3ztQG
DW Interview BTW Tino Chrupalla l Making Of
ምስል R. Oberhammer/DW

የዶቼ ቬለ ጋዜጠኞች ጉዞ

የፊታችን መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ,ም ጀርመን ሀገር አቀፍ ምርጫ ታካሂዳለች። ለዚህም የተለያዩ ቅስቀሳዎችን እና ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው። ምርጫው ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት ምርጫዎች በተለየ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ሆኗል። ላለፊት 16 ዓመታት ሀገሪቱን በመራሂተ መንግሥትነት ያስተዳደሩት እና በዜጎቻቸው እናታችን በሚል ቁልምጫ የጀርመንኛውን ሙተር የሚል የእናት ትርጉም ሙቲ እያሉ የሚጠሯቸው አንጌላ ሜርክል የሥልጣን ዘመናቸው ማብቅያ ነው። ይኽም ሀገሬውንም ሆነ የመገናኛ ብዙሃኑን በመሳቡ በመለኝነታቸው የሚወደሱት ቆፍጣናዋ ፖለቲከኛ ማን ይተካቸው ይሆን የሚለው የሁሉም መነጋገሪያ አድርጎታል። ከአፍሪቃው ክፍል የተውጣጡ የዶቼ ቬለ ጋዜጠኞችም ከሰሞኑ ወደተለያዩ የጀርመን ከተሞች በመጓዝ የምርጫውን ዝግጅት ይቃኛሉ፤ ይዘግባሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ