1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን መከላከያ ሚንስትር ውይይት በኮንጎ

ሐሙስ፣ መስከረም 18 1999

የጀርመን መከላከያ ሚንስትር ፍራንስ ዮሴፍ ዩንክ ------>

https://p.dw.com/p/E0i3
ዩንክ እና ፔምባ
ዩንክ እና ፔምባምስል AP

በአፍሪቃ ያደረጉትን የሦስት ቀናት ውይይት አብቅተው ትናንት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ዩንክ በጅቡቲ ያለውን የጀርመን ጦር ሠፈር ከጎበኙ በኋላ ወደ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክም ተጉዘው ነበር። ሚንስትሩ በኮንጎ ካካሄዱት ውይይት በኋላ ጀርመን ለኮንጎ የምትሰጠው፡ ለምሳሌ፡ የጦር ሥልጠናን የመሰለው ድጋፍ በዚያ ሁለተኛው ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ካበቃ በኋላ እንደማያበቃ አስታውቀዋል። ይሁንና፡ ቶማስ ኔልስ እንደዘገበው፡ በዚያ የሚካሄደውን ምርጫ ዋስትና ለማረጋገጥ በተሰማራው የአውሮጳ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጓድ ውስጥ የተሳተፉት 780 ጀርመናውያን ወታደሮች ተልዕኮ ከታቀደለት ጊዜ በላይ እንደማይራዘም አስታውቀዋል።