1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ምርጫ ዉጤና ሜርክል

ሰኞ፣ መስከረም 13 2006

የCDU እና የያኔዋ የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ (ምዕራብ ጀርመን) መሥራች ኮንራድ አደናወር ከ1949 እስከ 1960 ድረስ ለሰወስት ዘመነ-ሥልጣን በመራሔ-መንግሥትነት አገልግለዋል።ከአደናወር ቀጥሎ ለሰወስት ዘመነ-ሥልጣን በመራሔ መንግሥትነት የመሩት ሔልሙት ኮል ናቸዉ።ሜርክል ጀርመንን ለሰወስተኛ ዘመነ-ሥልጣን በመምራት ሰወስተኛዋ ይሆናሉ

https://p.dw.com/p/19mhg
German Chancellor and leader of the Christian Democratic Union (CDU) Angela Merkel drinks a glass of wine as she celebrates after first exit polls in the German general election (Bundestagswahl) at the CDU party headquarters in Berlin September 22, 2013. Merkel won a landslide personal victory in a German election on Sunday, putting her within reach of the first absolute majority in parliament in half a century, a ringing endorsement of her steady leadership in the euro crisis. REUTERS/Fabrizio Bensch (GERMANY - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ድልምስል Reuters

ለተቀናቃኞቻቸዉ አልምጥ፥ አድፋጭ፥ ለጠላቶቻቸዉ መሠሪ፥ ሻጥረኛ ናቸዉ።ለአድናቂ-አፍቃሪዎቻቸዉ ግን እናት አከል ናቸዉ።ሙቲ- ይሏቸዋል በቁልምጫ።ሌሎች አንጊ።የደጋፊ፥ አድናቂዎቻቸዉ ትልቅ መፈክር ከፓርቲያቸዉ ይልቅ ለሳቸዉ ያለመ ነበር።ለአንጌላ ሜርክል። «መራሒተ-መንግሥት እንደሆንን እንቀጥለለን።ዴር ሽፒግል የተሰኘዉ የጀርመን እዉቅ መፅሔት በፋንታዉ ጀርመንን እንዳለ ለሳቸዉ ሰጣቸዉ።«የሜርክል ሪፐብሊክ።»ብሎ።በምርጫዉ ደንብ ትናንት ያሸነፈዉ በርግጥ ፓርቲያቸዉ ነዉ።ክሪስቲያን ዲሞክራቲክ ሕብረት (CDU)።ድሉ ግን ያለ እሳቸዉ የሚታሰብ አልነበረም።የምርጫዉ ዉጤት፥ የሜርክል ሚና፥ የአሸናፊ፥ ተሸናፊ ፓርቲዎች ማንነት፥ ያፍታ ዝግታችን ትኩረት ነዉ።አብራችሁን ቆዩ።

ከሰላሳ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረዋል።አሸናፊዉ የእስካሁኑ ተጣማሪ መንግሥት ትልቅ ፓርቲ ነዉ።የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ሕብረት (CDU) እና የክርስቲያን ሶሻል ሕብረት (CSU በጀርመንኛዉ ምሕፃረ-ቃሉ።) ትልቁ ፓርቲ የትናንቱን አይነት ትልቅ ድል ሲያስመዘገብ ከ1990 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ነዉ) የትናንቱ የመጀመሪያዉ ነዉ።ካጠቃላዩ ድምፅ 41.5 ከመቶ።

ትልቁን ፓርቲ ለትልቅ ድል ያበቁት ከፓርቲዉ ዓለማና መርሕ ይልቅ የእሳቸዉ ስብዕና ነዉ።የወይዘሮ አንጌላ ሜርክል።ወጣት አድናቂዎቻቸዉ ሙቲ-የሚሏቸዉ የፖለቲካ ደጋፊዎቻቸዉ አንጊ፥ ሌሎች ብረቷ-እመቤት ይሏቸዋል።በድሉ ምሽት ዘፈኑ፥ ዘመሩ፥ ጨፈሩላቸዉም።

በ2008 የዓለም ልዕለ ሐያል፥ ሐብታሟን ሐገር ዩናይትድ ስቴትስን ያነገዳገደዉ የምጣኔ ሐብት ድቀት እስካሁንም የአብዛኛዉን የምዕራብ ዓለም ምጣኔ ሐብት እንዳሽመደመደ ነዉ።ከግሪክ እስከ አየር ላንድ፥ ከፖርቱጋል እስከ ስጳኝ እስከ ኢጣሊያ የሚገኙ ሐገር ደግሞ ከስረዉ፥ ብድርና ርዳታ እየጠየቁ ነዉ።

ፈረንሳይ እና ብሪታንያን የመሳሰሉ ትላልቅ ሐገራትም ግራ ቀኝ እየተላጉ ነዉ።ኪሳራ ባናወጠዉ ባሕር መሐል የምትቀዝፈዉ ጀርመን ሐይለኛዉ ነዉጥ ሳይነካት በነዉጡ የተጎዱትን በተለይ አዉሮጳዉያኑን በመርዳት፥ መደጎም ግንባር ቀደሟ ሐገር ሆናለችም።

ታላቁ ነዉጥ የዓለምን ፖለቲካዊ፥ ምጣኔ ሐብታዊ ሒደት የሚዘዉረዉን ሐያል ዓለም ግራ ቀኝ በሚያላጋበት ዘመን-ሁሉ የአዉሮጳን ትልቅ፥ ሐብታም፥ ጠንካራ ሐገር የመሩና የሚመሩት አንጌላ ሜርክል ናቸዉ።ሜርክል ሥልጣን የያዙት እትማማች የሚባሉት የጀርመን ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች (CDU/CSU) ከመሐል ግራዉ ከሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (SPD) ጋር በሁለት ሺሕ አምስት ታላቅ ተጣማሪ መንግሥት በሁለት ሺሕ አምስት ከመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ ነዉ።

ጀርመን ከአብዛኛዉ ተሻራኪዎችዋ በተለየ መንገድ ከምጣኔ ሐብቱ ድቀት አምልጣ ሌሎችን ለመርዳት የደረሰችበትን መርሕ-ሜርክል እንደ መራሔ መንግሥት አስፈፅመዉት ይሆናል።መርሑን ከቀየሱት አንዱ ምናልባትም ግንባር ቀደሙ ግን የያኔዉ የገንዘብ ሚንስትር ፒር ሽታይንብሩክ ነበሩ።ታላቁ ተጣማሪ መንግሥት በሁለት ሺሕ ዘጠኝ ከፈረሰ በሕዋላ ዋነኛ ተቃዋሚ የሆነዉን SPDን ወክለዉ በትናንቱ ምርጫ ለመራሔ መንግሥትነት ከሜርክል ጋር የተፎካካሩትም ራሳቸዉ ናቸዉ።ፒር ሽታይንብሩክ።

መራጩን ሕዝብ ያማለለዉ ጀርመንን ከምጣኔ ሐብት ኪሳራ ያዳነዉ መርሕ ቢሆን ኖሮ መርሑን ለመቀየስና እና ዋና ኪሳራዉ በደረሰት ወቅት የአዳኙ የመርሕ ዋና ተዋኝ የነበሩት ሽታይንብሩክና ፓርቲያቸዉ በሁለት ሺሕ ዘጠኙም፥ በትናንቱም ምርጫ ከሜርክሉ CDU የተሻለ ድምፅ ባገኙ ነበር።አላገኙም።እንዲያዉም ትልቁ ተቃዋሚ ፓርቲ SPD በረጅም ጊዜ ታሪኩ በጣም ዝቅተኛ ዉጤት ያመጣዉ በሁለት ሺሕ ዘጠኝ ነበር።ሃያ-ሰወስት ከመቶ ግድም።

እዉቁ የገንዘብ ባለሙያ ሽታይንብሩክ በመሩት በትናንቱ ምርጫ ያገኘዉ ድምፅ ከሁለት ሺሕ ዘጠኙ ሰወስት በመቶ ባልደረሰ ዉጤት የተሻሻለ ነዉ።ሃያ አምስት ነጥብ ስድት ከመቶ።ይሕ ዉጤት በፓርቲዉ ታሪክ ሁለተኛዉ ዝቅተኛ ዉጤት ነዉ።ሽታይን ብሩክ የልፋታችንን አላገኘነም ከማለት ሌላ-ሌላ ምክንያት አልነበራቸዉም።

«SPD ተጨባጭ እዉነት የሌለዉ የምርጫ ዘመቻ አላደረገም።ሥለ ፖለቲካ ተናገርናል።ብዙ ዜጎችም ሥለ ፖለቲካ እንዲወራ ይፈልጉ ነበር።ከሌሎቹ ፓርቲዎች የተሻለ የፖለቲካ መርሕ አቅርበናል ብዬም አምናለሁ።ይሁንና በግልፅ እንደሚታየዉ የምንፈልገዉን ዉጤት አላገኘንም።ከ2009ኙ የተሻለ ዉጤት አግኝተናል።ይሕ ግን በምርጫዉ እናገኘዋለን ብለን ላለምነዉ ዉጤት የሚበቃ አይደለም።»

በትናንቱ ምርጫ እጅግ የከፋዉ ለነጋዴዎችና ለባለ ኩባንዮች የሚወግነዉ የነፃ ወይም የለዘብተኛዉ ፓርቲ ዉጤት ነዉ።ከከሁለት ሺሕ ዘጠኙ ምርጫ በሕዋላ ሜርክል ከሚመራቸራቸዉ እሕትማማቾች ፓርቲዎች ጋር ተጣማሪ መንግሥት የመሠረተዉ የ(FDP) መሪዎች፥ የተጣማሪዉን መንግሥት ምክትል መራሔ መንግሥትነቱን ሥልጣን እንደያዙ ነዉ።

የምርጫዉ ዋና መሠረት ከስብዕና ይልቅ በመርሕ ላይ የተመሠረተ ቢሆን ኖሮ ከሁለት ሺሕ ዘጠኝ ጀምሮ ጀርመንን የመራዉ የተጣማሪዉ መንግሥት አባል ፓርቲዎች እንደየደረጃቸዉ የሕዝብ ድምፅ ባገኙ ነበር።አላገኙም።እንዲያዉም የተጣማሪዉ መንግሥትን የምክትል መራሔ-መንግሥትነትን፥ የዉጪ ጉዳይ፥ የምጣኔ ሐብት፥ የዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ሚንስትርነትን ሥልጣንን የመሳሰሉ ትላልቅ ሥልጣኖችን የያዘዉ የኤፍ ዴፔ ዉጤት አስደንጋጭ ነዉ።

ኤፍ ዴ ፔ በ1948 ከተመሠረተበት ወዲሕ የትናንቱን ያክል ዝቅተኛ ዉጤት አግኝቶ አያዉቅም። ከአምስት ከመቶ ያነሰ ድምፅ።በዚሕ ዉጤት አባላቱ ብሔራዊዉ ምክር ቤት ቡንደስታግ መግባት አይችሉም።ለመሪዎቹ፥ የፓርቲዉ የምርጫ ዘመቻ አስተባባሪ ራይነር ብሩደርለ እንዳሉት ከባድ ምሽት ነበር ትናንት።

«ዛሬ ከባድ ምሽት ነዉ።እስካሁን ድረስ ኤፍ ዴ ፔ አግኝቶት ከበረዉ ዉጤት ሁሉ የዛሬዉ በጣም መጥፎዉ መሆኑ ግልፅ ነዉ።ይሕ ለኤፍ ዴ ፔ በጣም ከባድ ጊዜ ነዉ።ለዚሕ (ዉድቀት) እንደ ዋነኛ ዕጩ ሐላፊነቱን እወስዳለሁ።የነፃነቱ ድምፅ ለወደፊቱ ሥፍራ እንዲያገኝ መጣር አለብን።የፓርቲዉ ፍፃሜ አይደለም፥ ሥራዉ ይቀጥላል።»

ሥራዉም፥ ፓርቲዉም እንደ ፓርቲ ይቀጥሉ ይሆናል።እስካሁን ግን የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሩ እስከ ሁለት ሺሕ አስራ-አንድ ድረስ የኤፍ ዴ ፔ ሊቀመንበር የነበሩት ጊዶ ቬስተርቬለ ናቸዉ።ምጣኔ ሐብታቸዉ ለከሰረዉ ለዩሮ ተጠቃሚ ሐገራት ጀርመን ከፍተኛዉን ድጋፍ እና ርዳታ ባደረገችበት፥ በከሰሩ ሐገራት ተከባ ምጣኔ ሐብቷ እንደጠከረ በቀጠለበት ባለፉት አራት አመታት የኢኮኖሚ ሚንስትርነቱን ሥልጣን የያዙት ያሁኑ የኤፍ ዴ ፔ ሊቀመንበር ናቸዉ።ፊሊፕ ሮዝለር።

ተጣማሪዉ መንግሥት የተከተለዉ ሠላማዊ የዉጪ መርሕ የመራጩን ልብ ማርኮ ቢሆን ኖሮ ከሜሪክል እኩል ባይሆን እንኳ ጊዶ ቬስተርቬለም የሕዝባቸዉን ከፍተኛ ድጋፍ ባገኙ ነበር።ተጣማሪዉ መንግሥት ጥቅል መርሑ ወይም የጀርመንን ምጣኔ ሐብትን ማሳደጉ፥ ዩሮን ከለየለት ኪሳራ ማዳኑ በትናንቱ ምርጫ ተፅዕኖ ማሳረፍ ቢችል ኖሮ የኢኮኖሚ ሚንስትሩ ከሜርክል እኩል እንኳን ባይሆን በተወደዱ ነበር።ግን አልሆነም።

እንዲያዉም በተቃራኒዉ ኤፍ ዴ ፔን ከምክር ቤት አባልነት አፈናጥሮ ትሎታል። ዉጤት ከቬትናም እናት አባት ተወልደዉ ጀርመን አድገዉ ምናልባት ትልቅ ሥልጣን በመያዝ የመጀመሪያዉ የዉጪ ዝርያ ያላቸዉ ፖለቲከኛ የሆኑትን የፓርቲዉን መሪ ፊሊፕ ሮዝለርንም ከሊቀመንበርነት ሥልጣን እንዲወርዱ አስገድዷቸዋል።

«(ለዉድቀቱ) ሐላፊነቱን እንደምወስድ ተናግሬያለሁ።ይሕ ማለት ዛሬ የነፃ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ ሊቀመንበርነቴን በፍቃዴ መልቀቄን ለፓርቲዉ አመራር አሳዉቄያለሁ።ይሕን በማድረግ ኤፍ ዴ ፔ በይዘትም፥ በሰብዕናም አዲስ መልክ እንዲኖረዉ መንገዱን እለቃለሁ ማለት ነዉ።»

የCDU/CSU የምርጫ ሥትራቴጂስቶች ወይም ሥልት ቀያሾች በርግጥ ዘይደዋል።«የምጣኔ ሐብት እድገት፥ ቀረጥ-ቅነሳ፥ የማሕበራዊ ድጎማ ጭማሪ፥ የዉስጥና የዉጪ መርሕ»፥ ከሚሉት ወይም የኤስፔደዉ ዕጩ እንዳሉት በጥቅሉ ፖለቲካ ላይ ከማተኮር ይልቅ ስብዕናን ነዉ የመረጡት።አንጌላ ሜርክልን።ሴትዮዋ-አንደኛ በመጀርመን ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት መሪ ናቸዉ።የዓለም ጠንካራዋ ሴት ናቸዉ።ለሜርክል ፓርቲ አብዛኛዉን ድምፅ የሰጡትም ሴቶች ናቸዉ።

አንዳድ የፖለቲካ ተንታኞች ነጥብ ለማጠራቀም (ድምፅ ለማግኘት) የሚያደቡ ይሏቸዋል።በርግጥም ብዙም የማይጠቅማቸዉን ብዙ፥ ሰጥተዉ በጣም የሚጠቅማቸዉን ትንሽ የመቀበልን ሥልት ተክነዉበታል።በተለይ አወዛጋቢ ጉዳይ ሲነሳ ሚንስትሮቻቸዉን ወይም የበታቾቻቸዉን አጋፍጠዉ ዉዝግቡ ቀዝቀዝ፥ አዋራዉ ሰከን ሲል አሸናፊዉን ሐይል ደግፈዉ ካደፈጡበት ብቅ የሚሉ ፖለቲከኛ ናቸዉ።

ኤስ ፔ ዴዎች በጌርሐርድ ሽሩደር መሪነት የመንግሥትነቱን ሥልጣን ይዘዉ በነበረበት ወቅት እራሳቸዉ ያረቀቁ፥ ያፀደቁትን አጀንዳ ሁለት ሺሕ አስር-የተባለዉን የቁጠባ መርሕ እራሳቸዉ በመቀበልና ባለመቀበል መሐል ተከፍለዉ ሲወዛገቡ «አንጊ» አፈፍ አድርገዉ ተጠቀሙበት። የፓርቲያቸዉ የምርጫ ሥልት ቀያሾች በሜርክል ሥብዕና ላይ ባተኮረዉ የምርጫ ዘመቻቸዉ ድል አደረጉ።በድሉ ኮሩ።ጨፈሩም።

«ፈንጠዝያዉ ሁላችንም መደሰት እንደምንችል መስካሪ ነዉ።ይሕ በርግጥ ፋና ወጊ ዉጤት ነዉ።ባለቤቴን ላመሰግን እወዳለሁ።ዉድ ወዳጆቼ፥ ሕብረቶቹ (CDU/CSU) የሕዝብ ፓርቲ መሆናቸዉን አሳይተናል።መጪዉ ዘመንም ለጀርመን የስኬት ጊዜ እንዲሆን በሚቀጥሉት አራት ዓመታት የምንችለዉን ሁሉ እናደርጋለን።ዛሬ ግን ድንቅ ሥራ በማከናወናችን እንደሰታለን።»

ተደስተዋል።የCDU እና የያኔዋ የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ (ምዕራብ ጀርመን) መሥራች ኮንራድ አደናወር ከ1949 እስከ 1960 ድረስ ለሰወስት ዘመነ-ሥልጣን በመራሔ-መንግሥትነት አገልግለዋል። ከአደናወር ቀጥሎ ለሰወስት ዘመነ-ሥልጣን በመራሔ መንግሥትነት የመሩት ሔልሙት ኮል ናቸዉ።ከ1982 እስከ 1998።ምሥራቅና ምዕራብ ጀርመንን በማዋሐዳቸዉ ዳግም የተዋሐደችዉ ጀርመን አባት በሚል ቅፅል የሚንቆለጳጳሱት ኮል እንደ አደናወር ሁሉ የCDU ፖለቲከኛ ናቸዉ።

የኮል ታማኝ አገልጋይ-ወይም የፖለቲካ ማደጎ ተደርገዉ የሚታዩት አንጌላ ሜርክል ጀርመንን ለሰወስተኛ ዘመነ-ሥልጣን በመምራት ሰወስተኛዋ ይሆናሉ።̎ከዚያ ለመድረስ ግን ከባድ ሥራ ይጠብቃቸዋል።እሳቸዉም ትናንት በድል የተደሰተዉ ደጋፊያቸዉ አላናግር ቢላቸዉ እንኳን ነገ-ሥራ አለ ነዉ-ያሉት።

«ዛሬ ደስታ ነዉ።ነገ ደግሞ ሥራ አለ።እዚሕ መድረክ ላይ የምታዩዋቸዉ በሙሉ ነገ-መሥራት አለባቸዉ።»

የጀርመን ፌደራላዊ ምክር ቤት ስድስት መቶ ሠላሳ መቀመጫዎች አሉት።አሸናፊዎቹ የሜርክል እትማማች ፓርቲዎች ያገኙት ሰወስት መቶ አስራ-አንድ መቀመጫ ነዉ።በዚሕ ዉጤት ብቻቸዉን መንግሥት መመሥረት አይችሉም።የእስካሁኑ ተጣማሪ ፓርቲ ኤፍ ዴ ፔ ደግሞ ምክር ቤት እንኳ መግባት አልቻለም።አንድ መቶ ዘጠና ሁለት መቀመጫ በማግኘት ሁለተኛዉን ደረጃ የያዘዉ ኤስ ፔ ዴ፥ በሥልሳ-አራት መቀመጫዎች የሰወስተኛዉን ደረጃ ከያዘዉ የግራዎች ፓርቲ እና በስልሳ ሰወስት መቀመጫዎች አራተኛዉን ደረጃ ከያዘዉ ከአረንጓዴዎቹ ፓርቲ ጋር ተጣማሪ መንግሥት መመስረት ይችላሉ።

ግን የተቀሩት ፓርቲዎች እስካሁን ባላቸዉ አቋም መሠረት ከግራዎቹ ፓርቲ ጋር መጣመር ሥለማይፈልጉ፥ ከትወራ በላይ ገቢር መሆኑ ሲበዛ አጠራጣሪ ነዉ።ሥለዚሕ ተጣማሪ መንግሥት የመመሥረቱ እድል አሁንም በመራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እጅ ነዉ።ሜርክል ደግሞ የወደፊቱ መንግሥት የተረጋጋ መሆን አለበት ባይናቸዉ።

«እኛ እንደ ሕብረት መንግሥት ለመሥረት ግልፅ ሐላፊነት አለብን።ጀርመን የተረጋጋ መንግሥት ያስፈልጋታል።ሥለዚሕ ይሕን ሐላፊነት ልንወጣ ይገባናል።»

ሐላፊነቱን ለመወጣት ያላቸዉ ምርጫ ሁለት ነዉ።አንድም የቀድሞዉን ታላቅ ጥምረት ከኤስ ፔ ዴ ጋር መመሥረት፥አለያም ከአረንጓዴዎቹ ጋር መጣመር ነዉ።ዛሬ ግን ወይዘሮዋ በርግጥ አሸንፈዋል።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

Chancellor candidate of German Social Democratic (SPD) party Peer Steinbrueck (R) gestures next to SPD's candidate in Hesse, Thorsten Schaefer Guembel at an election campaign event in Frankfurt am Main, Germany, on September 21, 2013. A total of 61.8 million people over the age of 18 will be able to vote on September 22nd to elect the next government of the European Union's most populous nation and biggest economy. AFP PHOTO / DANIEL ROLAND (Photo credit should read DANIEL ROLAND/AFP/Getty Images)
ሽታይን ብሩክ ክድጋፊዎቻቸዉ ጋርምስል Daniel Roland/AFP/Getty Images
Bildnummer: 60513814 Datum: 23.09.2013 Copyright: imago/Xinhua (130922) -- BERLIN, Sept. 22, 2013 (Xinhua) -- Philipp Roesler, chairmen of the Free Democratic Party (FDP), attends the FDP election event in Berlin on Sept. 22, 2013. The latest exit poll results showed Sunday that German Chancellor Angela Merkel s conservative Christian Democrats (CDU) and their Bavarian sister party the Christian Social Union (CSU) could have an absolute majority to govern without a coalition partner. (Xinhua/Stefan Zeitz) GERMANY-BERLIN-VOTE PUBLICATIONxNOTxINxCHN Politik people Bundestagswahl Wahl Wahlabend xas x0x 2013 quer premiumd 60513814 Date 23 09 2013 Copyright Imago XINHUA Berlin Sept 22 2013 XINHUA Philipp ROESLER Chairmen of The Free Democratic Party FDP Attends The FDP ELECTION Event in Berlin ON Sept 22 2013 The Latest Exit Poll Results showed Sunday Thatcher German Chancellor Angela Merkel S Conservative Christian Democrats CDU and their Bavarian Sister Party The Christian Social Union CSU Could have to absolute Majority to Govern without a Coalition Partner XINHUA Stefan Zeitz Germany Berlin VOTE PUBLICATIONxNOTxINxCHN politics Celebrities Federal election Choice Election evening x0x 2013 horizontal premiumd
ሮዝለር፤ ሥልጣን ለቀቁምስል imago/Xinhua
Free Democratic Party (FDP) top candidate Rainer Bruederle (L) and German Economy Minister and leader of the liberal FDP Philipp Roesler (R) address to members after first exit polls in the German general election (Bundestagswahl) in Berlin September 22, 2013. REUTERS/Fabian Bimmer (GERMANY - Tags: POLITICS ELECTIONS)
መርዶ-ብሩደርለ እና ሮዝለርምስል Reuters
BERLIN, GERMANY - SEPTEMBER 22: Supporters of the German Christian Democrats (CDU) react to initial results that give the CDU 42% of the vote in German federal elections on September 22, 2013 in Berlin, Germany. Germany is holding federal elections that will determine whether Chancellor Angela Merkel, who is also chairwoman of the CDU, will remain chancellor for a third term. Though the CDU has a strong lead over the opposition, speculations run wide as to what coalition will be viable in coming weeks to create a new government. (Photo by Clemens Bilan/Getty Images)
ፌስታምስል Clemens Bilan/Getty Images
German Chancellor and leader of the Christian Democratic Union (CDU) Angela Merkel smiles as she receives flowers from Hermann Groehe (R), CDU secretary general, after first exit polls in the German general election (Bundestagswahl) at the party headquarters in Berlin September 22, 2013. REUTERS/Fabrizio Bensch (GERMANY - Tags: POLITICS ELECTIONS)
«እንኳን ደስ አለዎት»ምስል Reuters
Supporters of the Christian Democratic Union (CDU) stand on a balcony behind a banner reading 'Angie', the nickname of German Chancellor and conservative Christian Democratic Union (CDU) leader Angela Merkel, as they celebrates after first exit polls in the German general election (Bundestagswahl) at the CDU party headquarters in Berlin September 22, 2013. Chancellor Angela Merkel won a landslide personal victory in a German election on Sunday, putting her within reach of the first absolute majority in parliament in half a century, a ringing endorsement of her steady leadership in the euro crisis. REUTERS/Kai Pfaffenbach (GERMANY - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ምስል Reuters
Supporters of the Christian Democratic Union (CDU) celebrate after first exit polls in the German general election (Bundestagswahl) at the CDU party headquarters in Berlin September 22, 2013. Chancellor Angela Merkel won a landslide personal victory in a German election on Sunday, putting her within reach of the first absolute majority in parliament in half a century, a ringing endorsement of her steady leadership in the euro crisis. REUTERS/Fabrizio Bensch (GERMANY - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ደጋፊያቸዉምስል Reuters

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ




ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ