የጀርመን ርዳታ ለኢትዮጵያ ድርቅ
ዓርብ፣ ጥር 13 2008ማስታወቂያ
የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የ41.3 ሚሊዮን ዩሮ ርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቀ። በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ለዶቼቬለ እንዳስታወቀው እርዳታውን በተለይ በድርቅ ለተጎዱት የአፋርና የሶማሊያ ክልል አካባቢዎች ለመስጠት ነው የታሰበው። የጀርመን መንግሥት ከለግሰው እርዳታ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ለአለም የምግብ ድርጅት የተወሰነውን ደግሞ ለተመ የህፃናት መርጃ ድርጅት እንደሚሰጥም ገልጿል። በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ ይሰጣል የተባለው ይኽው ርዳታ በተለይ ለነፈሰጡሮችና ለህጻናት የታሰበ መሆኑም ተጠቅሷል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ