1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ቡድን ሽንፈትና የአዲስ አበባ ደጋፊዎቹ

ዓርብ፣ ሐምሌ 1 2008

ለድል-ፌስታ ጭፈራ የተዘጋጁለትን ምሽት በሽንፈት ሐዘን እና ቁጭት ማሳለፍ ግድ ሆኖባቸዋል

https://p.dw.com/p/1JLw0
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

[No title]

ለወትሮዉ በፀሐያማዉ በጋ ሞቅ፤ ደመቅ፤ጣደፍ የሚሉት የጀርመን ከተሞች ዛሬ ቀዝቀዝ፤ ደብዘዝ፤ ብለዉ ነዉ የዋሉት። ምክንያት-እግር ኳስ።ፈረንሳይ ላይ የተያዘዉን የአዉሮጳ የእግር ኳስ ግጥሚያን ከዋንጫ ጋር ያጠናቅቃል ተብሎ የተጠበቀዉ የሐገሪቱ ብሔራዊ ቡድን ትናንት በፈረንሳይ ባላጋራዉ ሁለት ለባዶ መሸነፉ የጀርመን እግር ኳስ አፍቃሪን አንገት አስደፍቷል። አንዳዶች ሽንፈቱን «የኳስ ነገር» እያሉ ለመፅናናት ቢሞክሩም፤ የብዙዉን እግር ኳስ አፍቃሪን የስሜት ስብራት ለመጠገን የተከረዉ የለም። ሽንፈቱ፤ አዲስ አበባ ለሚኖሩ ጀርመናዉያንና ወዳጆቻቸዉም የሐዘን መርዶ ብጤ ነዉ-የሆነዉ።ግጥሚያዉን አንድ አዳራሽ ሆነዉ በቴሌቪዥን ሲከታተሉ የነበሩ እግር ኳስ አፍቃሪዎች ለድል-ፌስታ ጭፈራ የተዘጋጁለትን ምሽት በሽንፈት ሐዘን እና ቁጭት ማሳለፍ ግድ ሆኖባቸዋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አብሯቸዉ ነበር ያበር ያመሸዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ