1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ባለኃብቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ የተጠራ ጉባዔ

ዓርብ፣ ግንቦት 5 2008

ጀርመን በባየር ግዛት መዲና ሙኒክ ላይ ኢትዮጵያ ከአፍሪቃ አዲስዋ የንግድ መዳረሻ በሚል የአንድ ቀን ጉባዔ ተካሄደ። ኢትዮጵያንን ጨምሮ ወደ 140 ተሳታፊዎች የታደሙበት ይህ ጉባዔ በጀርመን የሚገኙ መዋለ ንዋይ አፍሳሾችን ለመሳብ እንደሆነም ተመልክቶአል።

https://p.dw.com/p/1InAl
München: Neues Rathaus im Abendlicht
ምስል picture-alliance/dpa


የኢትዮጵያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዮድሮስ አድኃኖም ይገኙበታል በተባለዉ በዚህ ጉባዔ ላይ ባይገኙም በኤኮኖሚ ጉዳይ ከፍተኛ ባለስልጣናት መገኘታቸዉ ነዉ የተገለፀዉ። ጉባዔዉ ከመጀመሩ በፊት ጀምሮ ግን ጉባዔዉን በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ እንደጋረደዉ ተመልክቶአል። እዚሁ ጉባዔ ላይ የተገኘዉን ባልደረባችን ማንተጋፍቶት ስለሺን አዜብ ታደሰ ዛሬ ከቀትር በኃላ ማለት ጉባዔዉ ከመጠናቀቁ በፊት አነጋግራዉ ነበር።


ማንተጋፍቶት ስለሺ


አዜብ ታደሰ