1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን እና ኢትዮጵያ ትብብር ስምምነት

ዓርብ፣ ነሐሴ 30 2006

ኢትዮጵያና ጀርመን የሁለትዮሽ ትብብር ዉል ተፈራረሙ። ትናንት የገንዘብ እና የኤኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴታ አቶ አህመድ ሽዴ እና የፌደራል ሪፑብሊክ ጀርመን የኤኮኖሚና ልማት ምክትል ሚኒስትር ቶማስ ዚልበርሆርን ለሁለቱ ሃገራት የተፈራረሙት የትብብር ዉል ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2015 እስከ 2018ዓ,ም የሚዘልቅ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1D7p7
ምስል DW/G. Tedla

በዚህ የልማት ትብብርም የአንድ መቶ አርባ ሚሊዮን ዩሮ ገደማ መመደቡ ተገልጿል። ጀርመንና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የልማት ትብብር ዉል ከጀመሩ 50 ዓመት ሆኗቸዋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የፊርማዉን ስርዓት ተከታትሏል፤ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ