1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የልማት እርዳታ ለኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ጥቅምት 24 2010

«የጀርመን መንግሥት እርዳታ በዋናነት ለትምሕርት ጥራት ለተግባረ ዕድ ትምሕርት እንዲሁም ለተፈጥሮ ጥበቃየሚውል ነው» የኢትዮጵያ የገንዘብ እና የኤኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ አቶ አድማሱ ነበበ ።

https://p.dw.com/p/2mzv2
Deutschland-Äthiopien Zusammenarbeit
ምስል Getachew Tedla HG

የጀርመን እና የኢትዮጵያ የልማት እርዳታ ስምምነት 

የጀርመን እና የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ በኢትዮጵያ ለተለያዩ የልማት ዘርፎች እርዳታ የሚውል የአንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን ዩሮ የእርዳታ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ተፈራረሙ። ለ3 ዓመታት የሚዘልቀው ይህ የጀርመን መንግሥት እርዳታ በዋናነት ለትምሕርት ጥራት ለተግባረ ዕድ ትምሕርት እንዲሁም ለተፈጥሮ ጥበቃ እንደሚውል ከኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብ እና የኤኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ አቶ አድማሱ ነበበ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በጀርመን የልማት እና የኤኮኖሚ ተራድኦ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከሰሀራ በስተደቡብ ያሉ የአፍሪቃ ሃገራት ክፍል ኃላፊ ዶክተር ሽቴፋን ኦስቫልድ የእርዳታው ዓላማ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት እና ጠንካራ ኢትዮጵያን ማየት መሆኑን ለዶቼ ቬለ አስረድተዋል። በፊርማው ስነ ስርዓት ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል። 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ