ኤኮኖሚ
የጀርመን እና የኢትዮጵያ የንግድ ጉባዔ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 22 2009ማስታወቂያ
በዚህ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ዶ/ር መብርሃቱ መለስ፤ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ኩማ ደመቅሳ ፣ሌሎች ሹማምንቶች ኢትዮጵያዉያን እና ጀርመናዉያን የንግድ ባለሞያዎች እና መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች እንዲሁም በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተገኝተዋል። ጎርጎረሳዊዉ 2016 ዓ,ም ኢትዮጵያ 177 ሚሊዮን ይሮ የሚያወጣ ሸቀጥን ለጀርመን ሸጣለች። ይህም ከ 2015 ዓም ጋር ሲነጻፀር በሁለት በመቶ ይበልጣል። ጀርመን ደግሞ በ2016 ማሽኖችንና የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 350 ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ ያላቸዉ እቃዎች ወደ ኢትዮጵያ ልካለች። ጀርመን ወደ ኢትዮጵያ ያስገባችው የንግድ ሸቀጥ በ 44 በመቶ ጨምሯል ። የሃኖቨሩ የጀርመን ኢትዮጵያ የንግድ ጉባዔ ዓላማ የኢትዮጵያ መንግሥት የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት እድሎችን ለጀርመን ባለሃብቶች እና ለጀርመን ኩባንያዎች ማስተዋወቅ ነዉ ተብሎአል፤ የጉባኤውን ሂደት የተከታተለው የዶይቼ ቬለ ጋዜጠኛ እሸቴ በቀለ በስልክ ጠይቀነዉ ነበር።
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሠ