1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ክፍለሃገራት ምርጫ ዉጤትና አስተያየት

ሰኞ፣ መጋቢት 5 2008

ቁልፍ በተባሉ በሦስት የጀርመን ፌዴራዊ ግዛቶች ትናንት በተደረጉ ምክር ቤታዊ ምርጫዎች «AfD» የተባለው እና የቀኝ ዘመሙ ለጀርመን አማራጭ ፓርቲ ባለ ሁለት አሐዝ ውጤት በማስመዝገብ የምክር ቤት ውክልናን አገኘ።

https://p.dw.com/p/1ICxq
Infografik Landtagswahl Baden-Württemberg Deutsch

በምሥራቃዊ ጀርመን የዛክሰን አንሃልት ፌዴራዊ ግዛት 24 በመቶ የመራጭ ድምፅ በማግኘት 30 በመቶ ያህል ድምፅ ካገኘው የክርስትያን ዴሞክራቶቹ ሕብረት ቀጥሎ ሁለተኛው ጠንካራ ቡድን መሆኑ፤ በጀርመን የፖለቲካዉን ሁኔታ ሳይዘዉረዉ እንዳልቀረ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ነዉ። የበርሊኑ ወኪላችን ትናንት በጀርመን ስለተካሄደዉ የክፍለሃገራት ምርጫ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ