የጀርመን ዉህደት 21ኛ ዓመት በዓል በቦን
ሰኞ፣ መስከረም 22 2004ማስታወቂያ
ዛሬ ግንቡ ከፈረሰ 21ኛ ዓመቱ በቀድሞዋ የምዕራብ ጀርመን ዋና ከተማ ቦን ሲከበር ቤቱ የቀረ ሰዉ የለም በሚያስብል መልኩ ለወትሮ ጭር የሚሉት ጎዳናዎች ብሩህ ፊት በተላበሱ ወገኖች ተሞልተዋል። በዓሉ በየዓመቱ በተለያዩ ፌደራል ግዛት የሚስተናገድ ሲሆን የዘንድሮዉ ባለተራ ዶቼ ቬለ ራዲዮ የሚገኝበት የኖርድራይን ቬስት ፋለን ግዛት ነዉ። ከተማዉ ደግሞ ቦን። ለበዓሉ ድምቀት የተለያዩ ዝግጅቶች ከቅዳሜ ዕለት አንስቶ ሲካሄዱ ቆይተዋል፤ ቦን ነፃነት፤ አንድነትና ፍስሐ በሚል መፈክር እንግዶቿን ማስተናገዱን ተያይዛዋለች። ዝግጅቱ ከሚከናወንባቸዉ አካባቢዎች በአንዱ የተገኘችዉ ባልደረባዬን አዜብ ታደሰን ከቀትር በኋላ ስለበዓሉ አከባበር ያየችዉን እንድታካፍለን በስልክ አነጋግሬያታለሁ።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ