1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጉብኝት በሰሜን አፍሪቃ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2004

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቨለ በሰሜን አፍሪቃ 3 አገሮችን ሲጎበኙ፤ አገራቸው ፤ የተለያየ እርዳታ እንደምታቀርብ ቃል ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/13gdy
ምስል dapd



ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት በዚህ ሰሞን ፣ የያኔው የቱኒሲያ ፈላጭ ቆራጭ ፕሬዚዳንት ዚኔ ኧል አብዲኔ ቤን ዓሊ፣ በህዝብ ግፊት ሥልጣናቸውን ለቀው ወደ ስዑዲ ዐረቢያ ከኮበለሉ ወዲህ ፤ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጎዶ ቬስተርቨለ፣ ወደ ሰሜን አፍሪቃ በመጓዝ ዛሬ ቱኒስ ላይ ጉብኝታቸውን ሲያጠቃልሉ፣ አስተዳደርን ለማሻሻል፤ ጋዜጠኞችን ለማሠልጠንና የትምህርት ማዕከላትን ለማደስ የሚረዳ 32 ሚሊዮን ዩውሮ እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል። ስለ ወጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የሰሜን አፍሪቃ ጉብኝትና፤ ጀርመን ስለምትሰጠው የእርዳታ ዓይነት፣ ወደ እስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ይልማ ኃይለሚካኤል
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሀመድ