1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ዓመታዊ የአዲስ ግኝት ጉዳይ ሽልማት፣

ረቡዕ፣ ኅዳር 25 2006

ሰው ፣ ለኅልውናው ፣ ለጤንነቱ እጅግ የሚያስፈልገው ነገር ካለ ፣ በጥሞና አስቦበት፣ ያን ለማግኘትም ሆነ ለመፈልሰፍ ፣ ማትኮሩ ፤ መጣሩና እንዲያም ሲል ማሳካቱ አይቀርም። የአንድ ነገር ግኝት ፣ ምንጩ የአንድ ነገር ተፈላጊነት ነው። በእንግሊዝኛ (

https://p.dw.com/p/1AT7B
ምስል Trumpf

Necessity is the mother of all inventions)የሚባለው ያለምክንያት አይደለም።በዚህ በመኻል አውሮፓ ፣ እንደሰሜናዊው የክፍለ ዓለሙ ጫፍ የከፋ ባይሆንም፤ ካሁን ጀምሮ በሚመጡት 3 ወራት ብርዱ እያየለ የሚቀጥልበት ፤ ዕለቱ ፣ ከቀትር በኋላ ፣ገና በ 10 እና 11 ሰዓት ገደማ ( እ ኢ ሰዓት አቆጣጠር ማለት ነው)የሚጨልምበት ወቅት ነው። ታዲያ ይህን ለአንዳንዶች ድብርት ጋባዥ የመሰለውን ጨለማ የሚበዛበትን ሰዓት ለመቀየር፤ ከተሜዎች፤ በቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ፤ በበርና ጓሮ በየጎዳናውም ቦግ ያሉና በሰማይ የሚያበሩ ከዋክብትን የመሰሉ ንዑሳን አምፑሎችን በሠፈር ዛፎች ላይ በማንጠልጠል፤ በረገፉ ቅጠሎች ምትክ፤ የተንቆጠቆጠ ብርሃን እንዲፈነጥቅ ሲያደርጉ መመልከት ይቻላል። እናም ድቅድቁን ጨለማ ወደ ንጋት የተለውጠ ሊያስመስሉት ይችላሉ።

Deutscher Zukunftspreis - Feste Leuchtstoff Scheiben aus Nitridosilikat
ምስል Ansgar Pudenz/Deutscher Zukunftspreis

ጀርመን ፤ በያመቱ፣ የመጪው ዘመን ብሩኅ ዕጣ ፈንታ የፈጠራ ውጤት ሽልማት(Deutsche Zukunftspreis) የተሰኘውን በአገር አቀፍ ደረጃ እንደምታዘገጅ የታወቀ ነው። የዘንድሮው ውድድር አሸናፊ(አሸናፊዎች ) ሽልማት ዛሬ ማታ በርሊን ውስጥ የሚሰጠው በሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ዮአኪም ጋውክ ነው።

(ይቀጥላል)

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ