1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የልማት ትብብር ሚኒስቴርና ኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 12 2004

በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድቤት ለአሽባሪዎች ድርጅት ድጋፍ በመስጠት በሚል የተከሰሱ ሁለት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ጥፋተኞች ናቸዉ ሲል ወስኗል።

https://p.dw.com/p/13XxI
GMF Logo BMZ deutsch Schlagworte: Global Media Forum 2011,Logo BMZ deutsch Beschreibung: BMZ Logo in englisch Format: Artikelbild Bildrechte: Verwertungsrechte im Kontext des Global Media Forums eingeräumt.
የጀርመን የልማት ትብብር ሚኒስቴርና ኢትዮጵያ


እስከ 18 ዓመት ሊያሳስር ይችላል በተባለዉ ክስ ጋዜጠኞቹ በመጪው ሳምንት ብይን ይጠብቃሉ። ከዚህ በተጨማሪ ጠጣሩን የፀረ ሽብር ህግ በመጣስ የተከሰሱ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችም የፍርድ ሂደት እንደቀጠለ ነው። ባለፉት ወራት የመንግሥትን አሠራር በሚነቅፉ ላይ ሲካሄድ የቆየውን መጠነ ሰፊ የመያዝና የማሰር ዘመቻ አስመልክቶ የጀርመን ፌደራል መንግሥት ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታን እንድታሻሽል ጥሪ አቅርቧል። አሁን የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ ቃል የገባውን 14 ሚሊዮን ዩሮ የእርዳታ ገንዘብ የሚሰጠውም ይህን ጥሪ ኢትዮጵያ ስትቀበል ብቻ ነው። ሉድገር ሻዶምስኪ እንደዘገበው ተችዎች  ይህ የጀርመን መንግሥት ያቀረበው ጥሪ በቂ አይደለም ይላሉ። ዘገባውን ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋየ ለገሰ