የጀርመን የምረጡኝ ክርክር መድረክ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 30 2005ማስታወቂያ
በየአዉራ ጎዳናዉ ዳር ላይ፤ ህዝብ በሚበዛባቸዉ አካባቢዎች እና በየህንፃዉ ላይ የተለጠፉት የተለያዩ ፓርቲዎች አርማ እና መፈክር የምርጫዉ መዳረስን እያሳሰቡ የኛ የፖለቲካ መርኅ ይሻላል የሚለዉን ሃሳብ እያስተላለፉ ይገኛሉ። የአካባቢ ቀበሌዎችም የምርጫዉን ቀንና ህዝቡ ድምፅ የሚሰጥበትን ቦታ የሚጠቁም አድራሻን መምረጥ ለሚችለዉ ለየእያንዳንዱ ዜጋ ሁሉ በፖስታ አድራሻዎች አድርሰዋል። ይህን ሁሉ ተከትሎ የምርጫዉን ቀንና በተለይ ዉጤቱን ለመስማት በጉጉት የሚጠባበቀዉ ጥቂት አይደለም። ከጥቂት ዓመታት በፊት በጀርመን የተጀመረዉ የእጩ መራኄ መንግስታት የሚያካሂዱት የቀጥታ የቴሌቭዝን ስርጭት ክርክር በርካታ የጀርመን ነዋሪዎችን እንደ እግር ኳሱ ሁሉ በቴሌቭዝን መስኮት ዙርያ አሰባስቦ ስለ አገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካና የወደፊት ጉዞዉ አወያይቶአል። በጀርመን የሁለቱ እጩ መራሄ መንግስታት ያካሄዱትን የቀጥታ የቴሌቭዥን ክርክር በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እንዴት ተመለከቱት? ይህ ዓይነቱ ልምድስ መቼ ጀመረ? የዕለቱ የዝግጅታችን የሚያተኩርበት ርእስ ነዉ፤ የድምጽ ማዳመጫዉን በመጫን ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ።
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ