1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የምርጫ አካሄድና አስተምህሮቱ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 21 2005

የፊታችን መስከረም ለሚካሄደው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻ ላይ ናቸው። ፓርቲዎቹ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ ይረዳል ባሉት መንገድ የመራጩን ህዝብ ቀለብ ለመሳብ እየጣሩ ነው።

https://p.dw.com/p/19Xat
ምስል picture-alliance/ZB
Angela Merkels Wahlkampfauftritt am Samstag 24. August 2013 in Bonn
አንጌላ ሜርክልምስል DW/M. Lütticke
SPD-Kanzlerkandidat Peer Steinbrück
ፔር ሽታይንብሩክምስል picture-alliance/dpa

መስከረም 12 ፣ 2006 በጎርጎሮሳውያኑ መስከረም 22 2013 ዓም በጀርመን አጠቃላይ ምርጫ ይካሄዳል ። ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ በቀረው በዚህ ምርጫ የሚሳተፉ ከ 30 የሚበልጡ እውቅና ያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚቀጥሉት 4 ዓመታት እናከናውናለን የሚሉትን መርሃ ግብራቸውን እያስተዋወቁ ነው ። በአሁኑ ሰዓትም በዋነኞቹ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የቃላት ጦርነቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። ለረዥም ጊዜ ጀርመን የኖሩትና እዚሁ ጀርመን የተማሩት የህግ ባለሞያና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራ ሸዋ እንዳሉት ምንም እንኳን ከ30 በላይ ፓርቲዎች ለውድድር ቢቀርቡም አሸንፈው በጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መቀመጫ ሊያገኙ የሚችሉት ከ6 ወይ ከ 7 አይበልጡም ። ዶክተር ለማ እንደዘረዘሩት እነዚህን ፓርቲዎች በአሁኑ የምርጫ ዘመቻ የሚያከራክሯቸው ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች 6 ናቸው ።በምርጫ ዘመቻቸው ከነዚህ ወሳኝ የመከራከሪያ ርዕሶች የተለዩ ሃሳቦችን የሚያነሱ ፓርቲዎችም አሉ ።ከዋነኛዎቹ የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመራሄ መንግሥትነት የሚወዳደሩት የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ እጩ የቀድሞው የገንዘብ ሚኒስትር ፔር ሽታይንብሩክና የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲ እጩ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የምርጫ ዘመቻውን በሰፊው ተያይዘውታል ። የፊታችን እሁድ ደግሞ ፊት ለፊት የቴሌቪዥን ክርክር ያካሂዳሉ ። ፔር ሽታይን ብሩክ ከአሁኑ በቀደመው የጀርመን ጥምር መንግሥት በአንጌላ ሜርክል ካቢኔ የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ያከበተ ልምድ ያላቸው የፖለቲከኛ ናቸው ።
ጀርመን በዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ቀውስ ሳትጎዳ እንድታልፍ በማድረግ የሚመሰገኑት ለ 3ተኛ የሥልጣን ዘመን የሚወዳደሩት የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በህዝብ አስተያየት መመዘኛ መሠረት ተቀናቃናቸውን የሶሻል ዲሞክራቶቹን ፓርቲ እጩ ፔር ሽታይንብሩክን ለወራት በ 30 ነጥብ ሲመሩ ቆይተዋል ። ይሁንና አሁንም የመጨረሻ መፍትሄ ያልተበጀለት የግሪክ የገንዘብ ቀውስ ሜርክልን ችግር ውስጥ ሊጥል እንደሚችል እየተነገረ ነው ።
ዶክተር ለማ የጀርመን የምርጫ ዝግጅትና አካሄድ ዲሞክራሲን ተግባራዊ እናደርጋለን ለሚሉ አዳጊ አገሮች አርአያነቱ የጎላ መሆኑን ይናገራሉ ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ