1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የዉህደት ቀን አከባበር

ሐሙስ፣ መስከረም 25 1999

የጀርመን የዉህደት ቀን በተከበረበት (23.01.99) እለት መረሂተ መንግስት አጌላ መርክል ነጻነት ለጀርመን የወደፊትን እጣ ፈንታ የያዘዉ ትልቅ ትርጓሜ መሆኑን አጉልተዋል።

https://p.dw.com/p/E0hy
ምስል AP

በሰሜናዊ ጀርመን በኪል ከተማ በተደረገዉ የዉህደት ቀን የአከባበር ስነስርአት ላይ መራሂተ መንግስቷ አገራቸዉ የነጻነትን ሃይል እንደተሸከመች መሆንዋን በማከል ገልጸዋል።

የጀርመን የዉህደት ቀን ለመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ብርካታ ትዉስታዎችን ቀስቅሶአል። የምስራቅ እና በምዕራብ ጀርመንን ለያይቶ የነበረዉ ግንብ መፍረስ እና፣ የመወሃዱ ሂደት ትዉስታ! የቀኑም የፖለቲካ ሂደት በአብዛኛዉ ስለዚሁ ዉህደት ቀን አዉስቶ ቢዉልም ሜርክል በንግግራቸዉ የቻይና ትልቁ ኤሌክትሮኒክስ ኤንዱስትሪ ቤንኪዉ እና የጀርመኑ ሲመንስ መካከል ያለዉን ችግር እንዲፈታ፣ በሃይማኖት መካከልም ሆነ፣ በሃይማኖት ሰበብ የሚመጡትን ዉጥረቶች በሰላም መፍታት እንዲቻል በንግግራቸዉ ሳይጠቁሙ አላለፉም። ከቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመን የመጡት አንጌላ ማርክል የራሳቸዉን ምሳሌ በመዉሰድ ከትምህርት ቤት ጀምሮ በመቀጠል ሰላማዊ በነበረዉ የምስራቅ ጀርመኑ አብዮት አስከ አሁንዋ አንድ ስለሆነችዋ ጀርመን ሂደት አዉስተዋል። ሜርክል በመቀጠል..
«ጀርመን በተዋሃደች ግዜ በግልጽ እና በይፋ ዉጪ! ብሎ የጻፈልኝ ሰዉ ነበር። እኔም ዛሪ ለአራችን በግልጽ እና በይፍ እንዉጣ እላለሁ። በአገራችን አስጊ ከሆነ ነገር ይልቅ፣ ትልቅ ተስፋን እያየን ነዉ። ለአንድነት እና ለፍትህ መሳካት ዉስጣችን ያለዉን የነጻነት ሃይል መቀስስ አለብን። አገራችን ያጠነከራትን ሃሳቦችን በማፍለቅ ምስሎችን በመቅረጽ ችሎታ፣ ለአባት አገር ጀርመን ለእድነት፣ ለነጻነት ለአንድነት እንዲሆንም እናደርጋለን!»

በአሉ ስነስርአት የኪል ከተማ ግዛት የሆነችዉ የSchlezwig-Holsteins አገር አስተዳደር Peter Harry Carstensen በንግግራቸዉ ላይ...
«የምስራቅ ጀርመን ነዋሪዎች በችግር ዉስጥ በማለፍ በጥንካሪ ሰርተዋል። ስለዚህም ከፍተኛ ከበሪታ ሊሰጠዉ የሚገባ ጉዳይል ነዉ። የምዕራብ ጀርመን ነዋሪዎችም በጣም በሚያስደንቅ ሁኔታ አንድነታቸዉን እና ትብብራቸዉን አሳይተዋል። ይህም ሌላ ከበሪታ የሚሰጠዉ ጉዳይ ነዉ። እንደኔ አስተሳሰብ፣ ስለ የጀርመን አንድነት ሲታሰብ እነዚህን ሁኔታዎች ማስታወሰ ወይም ማጤን ይገባናል»
Oktober 3 በኪል ከተማ ታስቦ በዋለዉ የጀርመን የዉህደት ቀን በአል ላይ 1200 በላይ ጥሪ የተደረገላቸዉ፣ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ ከኢኮኖሚዉ ዘርፍ የመጡ ማህበረሰቦች፣ የቀድሞ የአገሪቷ ተጠሪዎች፣ የዉጭ ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል። የበአሉ አከባበር በጸሎት ፕሮግራም ጀምሮ፣ የተለያዩ ተወካዩች ንግግር አድርገዋል። ነጫጭ በሆኑ አስራድስት ድንዃኞች የ16 ስድስቱም የጀርመን ፊደራል ክልልን በመወከል ድርጅቶች የተለያዩ ነገሮችን ለእይታ አቅርበዋል።