1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ጦር የሶርያ ተልዕኮ

ዓርብ፣ ኅዳር 17 2008

ራሱን እስላማዊ መንግሥት ሲል የሚጠራው ቡድን ፓሪስ ላይ ጥቃት ከሰነዘረ እና በርካታ ሰዎችን ከገደለ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራትም በዚህ ቡድን ላይ ርምጃ እንዲወስዱ ፈረንሳይ እየጠየቀች ነዉ።

https://p.dw.com/p/1HDkr
Frank-Walter Steinmeier und Ursula von der Leyen
ምስል Reuters/H. Hanschke

[No title]

በዚህም ጥያቄ መሠረት፣ ጀርመን ፈረንሳይ ሶርያ ውስጥ በጀመረችው ትግል ላይ ከጎኗ እንደምትቆም የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ትናንት በበርሊን ይፋ አድርገዋል። አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ውሳኔውን አውግዘዋል። የጀርመን መከላከያ ሠራዊት ወይም «ቡንደስቬር» በዚህ በሶርያ በተጀመረው ትግል ውስጥ የሚኖረው ሚና ምን ሊመስል እንደሚችል በርሊን የሚገኘው ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል የላከው ዘገባ በአጭሩ ቃኝቷል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ