1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪዉ የጀርመን የመከላከያ ሚንስትር ከፓርቲ ሀላፊነት መልቀቅ

ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2012

የጀርመን የመከላከያ ሚንስትር አነግሬት ክራምፕ ካረንባወር ከፖለቲካ ኃላፊነታቸዉ መልቀቃቸዉን በትናንትናዉ ዕለት አስታዉቀዋል። የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ካረንባወር መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርከልን ይተካሉ ተብሎ ሲጠበቁ  ትናንት የወሰዱት ድንገተኛ ርምጃ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

https://p.dw.com/p/3Xcxs
Deutschland CDU-Chefin fordert von SPD und Grünen neuen Kandidaten in
Erfurt
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Sohn

ዉሳኔዉ ሜርከልን ጨምሮ ብዙዎችን አስደንግጧል

 
የጀርመን የመከላከያ ሚንስትር አነግሬት ክራምፕ ካረንባወር ከፖለቲካ ኃላፊነታቸዉ መልቀቃቸዉን በትናንትናዉ ዕለት አስታዉቀዋል። የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ካረንባወር መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርከልን ይተካሉ ተብሎ ሲጠበቁ  ትናንት የወሰዱት ድንገተኛ ርምጃ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ሚኒስትሯ አዲሲቱን የአውሮጳ ሕብረት ፕሬዝዳንት ኡርዙላ ፎንዴርላየንን ተክተዉ በጎርጎሮሳዊው ሐምሌ 2019  የጀርመን መከላከያ ሚንስትርነቱን ሥልጣን የያዙ ሲሆን ከክርስቲያን ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪነታቸውም ሆነ ከቀጣይ እጩ መራሂተ መንግሥትነታቸው ራሳቸዉን ማግለላቸዉ ሜርከልን ጨምሮ ብዙዎችን አስደንግጧል። ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ወገኖች የፖለቲከኛዋ ርምጃ ከፓርቲያቸው ፖለቲካዊ ጨዋታ ጋር ይገናኛል ባይ ናቸው።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ፀሀይ ጫኔ

ሽዋዬ ለገሰ