1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጅቡቲ ምክር ቤታዊ ምርጫ

ዓርብ፣ የካቲት 15 2005

አሊ ባራካት እንዳሉት በዚህ ምክር ቤታዊ ምርጫ ተቃዋሚዎች የሚያሸንፉ ቢመስልም በዚህ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች በብዙ መልኩ ልዩነት እንደሚታይባቸው ይነገራል። መሪዎቻቸውም ቢሆኑ በእድሜ የገፉ ናቸው።

https://p.dw.com/p/17kMq

እአአ ከ1999 ጀምሮ ጅቡትን እየመሯት ያሉ ፕሬዚዳንት ኡስማኤል ኡመር ጉሌህ ከአስርት ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጪው ምክር ቤታዊ ምርጫ ጠንካራ ተቃዋሚች እንደሚገጥሟቸው ተነግሯል። ምክር ቤታዊ ምርጫው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወከሉበት እንደሚሆንም ይገመታል። ገመቹ በቀለ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ከእስር ዓመታት በኋላ የጅቡቲ ተቃዋሚ ቡድኖች አንድ ላይ ሆነው ሀገሪቷን ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን እያስተዳደሯት ያሉትን ፕሬዚዳንት ኡስማይል ኡመር ጉሌህን ለመቀናቀን ወስነዋል። ተቃዋሚዎች እአአ በ2003 ከተደረገው ምርጫ በኋላ፣ ፍትሐዊነት ይጎለዋል ባሉት ምርጫ መሳተፍ አልፈለጉም ነበር። በጅቡቲ ላናሲዮን የተሰኘው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አሊ ባራካት እንዳሉት ተቃዋሚዎች አሁን አቋማቸውን ለውጠዋል፣

Djibouti President Ismail Omar Guelleh is seen during the closing conference of the the 24th Africa-France summit held in Cannes, France on February 16, 2007. Pool photo by Ludovic +++(c) dpa - Report+++
ጉሌሕምስል picture-alliance/ dpa
Djibouti map, highlighted, with surrounding countries, on texture,
ምስል AP



«ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊወከሉ የሚችሉበት ምክርቤታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው። ይህም የፖሊቲካ ፓርቲዎች እስከ ዛሬ ያደርጉት እንደነበረው ከምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን ትተው፣ በምርጫው በሰፊው እንዲሳተፉ አድርጓቸዋል። »

ጅቡቲ እአአ በ1977 ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣት ወዲህ ፕሬዝዳንት ጉሌህ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት ናቸው። በሚያዚያ 2011 ለሶስተኛ ዙር ከመመረጣቸው በፊት በስልጣን ሊያቆያቸው የሚችል የህገ መንግስት ማሻሻያ አድርገዋል። ተቃዋሚዎች አንሳተፍበትም ያሉትን ይህን ምርጫ ጉሌህ በ80 በመቶ ድምጽ አሸንፈዋል። ፓርቲያቸው ሁሉንም፣ ማለትም ስድሳ አምስቱን የፓርላማ መቀመጫ ተቆጣጥሯል።


ባለፈው ዓመት ጥር ወር በጅቡቲ ዋና ከተማ ምርጫ የፕሬዚዳንት ጉሌህ ፓርቲ በአንድ ነጻ የግል ተወዳዳሪ መሸነፉ ፓርቲው ላይ ያልታሰበ ስጋት አሳድሯል። ዛሬ ለሚካሄደው የምክር ቤት ምርጫም የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያላቸውን ልዩነት አጥበው ሰብዓዊ መብትና ነጻ ሚዲያን ማሻሻል እና ጎሰኝነት፣ ሙስናና በዝምድና መጠቃቀምን የማስወገድ የጋራ እቅዶቻቸው ላይ ተስማምተዋል። ለዚህ ይመስላል የላናሲዮን ዋና አዘጋጅ አሊ ባራካት ተቃዋሚዎች ምርጫውን እንደሚያሸንፉ የገመቱት፣

«በዚህ ምርጫ ዘመቻ እንደ ታዘብነው የተቃዋሚዎች ወገን የሚያሸንፍ ይመስለኛል።»

አሊ ባራካት እንዳሉት በዚህ ምክር ቤታዊ ምርጫ ተቃዋሚዎች የሚያሸንፉ ቢመስልም በዚህ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች በብዙ መልኩ ልዩነት እንደሚታይባቸው ይነገራል። መሪዎቻቸውም ቢሆኑ በእድሜ የገፉ ናቸው።

በምርጫው በሰፊው እንዲሳተፉ አድርጓቸዋል። »

ከጅቡቲ መንግስት ወገን ግን አዎንታዊ እርምጃ እየታየ ነው። ምርጫውን ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንዲሳተፉበት የጋበዘው መንግስት ግልጽ አሰራር እንደሚከተል አሊ ባራካት ገምተዋል፣

«ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የምርጫውን ሂደት እንዲከታተሉ ጥሪ ያቀረበው የጅቡቲ መንግስት መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁ። ሊጋዝ የተባለው የአከባቢው ቡድን፣ የአፍሪቃ ህብረት፣ የዓረቡ ሊጋ እና ሌሎች ድርጅቶችም ምርጫውን ለመታዘብ እዚህ ይገኛሉ። እና የሀገሪቱ መንግስት በምርጫ ሂደቱ ላይ ግልጽ አሰራር ይከተላል ብዬ አስባለሁ።»

ጅቡቲ ከአንድ ሚሊዮን በታች ህዝብ ያላት ትንሽ ሀገር ብትሆንም በምስራቅ አፍሪቃ ትልቅ ስልታዊ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላት ሀገር ናት። ፈረንሳይና ዩናይትድ ስቴትስም ከአፍሪቃ ትልቁ የጦር ሰፈር ያሏቸው ጅቢቲ ውስጥ ነው።

A soldier from Djibouti stands guard as The Koeln, a frigate in the German Navy, arrives at the Port of Djibouti, in Djibouti, Sunday, Jan. 27, 2002. Six more German ships arrived on Sunday to join the frigate Bayern , to support Operation Enduring Freedom. The German ships will be stationed in Djibouti and will monitor sea traffic from Red Sea and Persian Gulf. (AP Photo / Sayyid Azim)
ምስል AP

ገመቹ በቀለ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ