1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጆርጅ ቡሽ ታሪካዊ ጉብኝት በቬየትናም

ረቡዕ፣ ኅዳር 6 1999

የአሜሪካዉ ፕሪዝደንት ጆርጅ ቡሽ ከነገ በስትያ አርብ ቬየትናምን እንደሚጎበኙ ተገለጸ

https://p.dw.com/p/E0hh
ቬየትናም
ቬየትናምምስል AP/DW


የአሜሪካዉ ፕሪዝደንት ጆርጅ ቡሽ ከነገ በስትያ አርብ ቬየትናምን እንደሚጎበኙ ተገለጸ። የቀድሞዉ የአሜሪካ ፕሪዝደንት ቢል ክሊንተን በአሜሪካ ታሪክ እ.አ አቆጣጠር 2000 አ.ም ቬትናምን ለመጀመርያ ግዜ ከጎበኙ በኳላ፣ ጆርጅ ቡሽ የሚያደርጉት፣ ይህ ጉብኝት ለሁለተኛ ግዜ መሆኑም ታዉቋል።

የዩኤስ አሜሪካ ፕሪዝደንት ጆርጅ ቡሽ በቬየትናሙ ጉብኝታቸዉ አስታከዉ ሃያአንድ አገራት በሚሳተፉበት የእስያ እና የሰላማዊዉ ዉቅያኖስ አዋሳኝ አገሮች የኢኮኖሚ ትስስር ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ታዉቋል። ህዳር 12 በቬየትናም ዋና መዲና ሃኖይ በሚካሄደዉ የእስያ እና የሰላማዊዉ ዉቅያኖስ አዋሳኝ አገሮች የኢኮኖሚ ትስስር (APEC) ጉባኤ ላይ በኢኮኖሚ ጥያቄዎች ዙርያ ዉይይት ቢደረግም የሰሜን ኮርያ የአቶም ቦምብ ሙከራ፣ አሸባሪዎችን መዋጋት፣ ለጆርጅ ቡሽ ዋና የመወያያ ርእሳቸዉ እንደሚሆን የደህንነት አማካርያቸዉ Stephen Hadley ገልፀዋል።
«ፕሪዝዳንት ቡሽ ባለፉት ሶስት አመታት የስራ ግዜአቸዉ የእስያ እና የሰላማዊዉ ዉቅያኖስ አዋሳኝ አገሮች የኢኮኖሚ ትስስር አባል አገራት ከንግድ እና ከኢኮኖሚዉ እርዕስ ሌላ የጸጥታ ጥበቃ ዋናዉ የመነጋገርያ እርዕሳቸዉ አድርገዉት ቆይተዋል። አሁንም ቢሆን ለቡሽ አሸባሪዎችን ማደን እና መዋጋት ዋና እርእስ ሆኖ ይቆያል።» ባይ ናቸዉ።

በጸጥታ ጥበቃ ዙርያ እርዕስ ስር የጅምላ ጨራሽ መሳርያዎች ምርትን መግታት ዋናዉ እርዕስም ይሆናል። የሰሜን ኮርያ ባለፈዉ መስከረም ወር መጨረሻ የአቶም ቦንብ መሞከርዋ፣ የፒዮንግ ያንግ መንግስት የስድስትዮሹን ድርድር ችላ የማለቱ ጉዳይ፣ የፊታችን ማክሰኞ፣ በቬትናም፣ ሃኖይ የሚደረገዉ ጉባኤ በሚቀርበዉ የመነጋገርያ አጀንዳ ላይ የመጀመርያ እርዕስ እንደሚሆን ይጠበቃል። ቡሽ የቪየትናሙን ጉብኝታቸዉን አስታከዉ ከቻይናዉ ፕሪዝደንት Hu Jintao, ከራሽያዉ ፕሪዝደንት Putin እና ከደቡብ ኮርያዉ ፕሪዝደንት Roh ጋር፣ የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ንግግር እንደሚያደርጉም ታዉቋል።
ስለ እስያ (APEC) ጉዳይ አዋቂ እና የብሄራዊ ጥበቃ ምክርቤት ባልደረባ የነበሩት Douglas Paal በቬትናም ስለሚደረገዉ ዉይይት ሲገልጹ

«ሃያ አንዱ የእስያ እና የሰላማዊዉ ዉቅያኖስ አዋሳኝ አገሮች፣ የኢኮኖሚ ትስስር በጉባኤዉ ማጠናቀቅያ ላይ፣ በሰሜን ኮርያን በሚመለከት በወጣዉ ማዕቀብ ቁጥር 1718 መልሶ የሚያንጸባርቅ ብቻ ሳይሆን፣ እስካሁን ሰሜን ኮርያን በመቃወም ማዕቀብ ያላደረጉ አገሮች የሚያካተቱበት የፖለቲካ እገዳ ዉል ይፈጸማል።»

የቀድሞ የአሜሪካ በቪየትናም ወረራ፣ ቡሸ ቪየትናምን በሚጎበኙበት ወቅት ሌላዉ የመነጋገርያ እርእሳቸዉ ይሆናል። የኮሚኒስቱን ስርአት የምታራምደዉ ቪየትናም በደቡባዊ ምስራቅ እስያ አሉት ከሚባሉት አገራት መካከል የኢኮኖሚ እድገቷ በፈጣን ለዉጥ በማሳየቷ በቅርቡ የአለም የንግድ ድርጅት አባል ሆናለች። ሌላዉ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸዉ ሶስት የቬትናም ተዋላጅ፣ የሃኖዩን መንግስት በመቃወም የታሰሩበትም ድርጊት፣ የቡሽ አንዱ የሚነጋገሩበት እርዕስ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኮንደሊዛ ራይስ እስረኞቹን ለማስፈታት ከፕሪዝደንቱ ጋር አብረዉ እንደሚጓዙ ታዉቋል። ቩሽ እግረ-መንገዳቸዉን ሲንጋፖርን እና ኢንዶኔዝያን እንደምጎበኙም ታዉቋል።