1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገሀዱ ዓለም ገጽ

እሑድ፣ መጋቢት 29 2011

ስድስተኛው የጉማ ፊልም ሽልማት ባለፈው ሳምንት ተካሄዷል። ይህ በየዓመቱ የሚካሄደው ሽልማት እንደወትሮው ሁሉ በተለያዩ የፊልሙ ዘርፍ ለአሸናፊዎች ሽልማት አበርክቷል።

https://p.dw.com/p/3GMAU
Meseret Mekonnen Movie Makeup Artist
ምስል Privat

በጉማ ፊልም ሽልማት በገጽ ቅብ አሸናፊ መሠረት መኮንን 

የፊልም ተዋናዩን ወይም ተዋናይቱን ገጽ በመቀየር በፊልሙ ታሪክ ላይ ሕይወት ይዘሩበታል፤ አዛውንት፣ የተጎዳ፣ የታመመ፣ እና ሌሎችም መሰል ገጸ ባህሪያትን አስመስሎ በማዘጋጀት ከፊልም ባለሙያዎች ጋር በጋራ ይሠራሉ፤ የፊልም የገጽ ቅብ ባለሙያዎች ማለትም (Makeup) አርቲስቶች።  
በየፊልሙ የሚሳተፉትን ተዋንያን በገጽታም ሆነ በአካል ገጸ ባህሪውን መስለው ለመተወን እንዲችሉ የገጽ ቅብ ባለሙያ (Makeup Artist) ድርሻ የጎላ ነው ይሏቸዋል። ተዋናዩ በፊልሙ ደራሲ ከቀረጸው ገፀባህሪ ጋር ፍፁም እንዲመሳሰል በሚያደርጉት ጥረትም፤ የተመልካቹን ስሜት ልክ በገሀዱ ዓለም ያለ ያህል እንዲይዝ ያደርጋሉ።
በኢትዮጵያም በፊልሞቻችን በገጽ ቅብ ማለትም (Makeup) እድገት እየታየ መጥቷል ትላለች መሠረት መኮንን የፊልም ሜክአፕ ባለሙያ። ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገው የጉማ ፊልም ሽልማት በሲመት ፊልም የገጽ ቅብ አሸናፊ ሆናለች። 


ነጃት ኢብራሂም 

Meseret Mekonnen Movie Makeup Artist
ምስል Privat

ሸዋዮ ለገሰ