1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገና በዓል ልዩ ዘገባ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 15 2008

የጎርጎሪዮስን የቀን ቀመር የሚከተሉ በመላው ዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች በዛሬው ዕለት የክርስቶስ መወለድን በማክበር ላይ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/1HTr7
Bildergalerie Weihnachtsbeleuchtung
ምስል picture alliance/AP Photo

[No title]

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርእሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ የገና ቃለ-ቡራኬያቸውን አስምተዋል። ቡራኬያቸውንም ለከተማዋ ሮም እና ለመላው ዓለም የተለመደውን «ኡርቢ፥ ኤት ኡርቢ» በማለት ለሦስተኛ ዓመትም ዛሬ በካቶሊክ ዋና መቀመጫ ቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ ሠገነት ላይ ሆነው አሰምተዋል። በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰውን ምዕምን አውቶማቲክ ጠመንጃዎችን የታጠቁ ጸረ-ሽብር የጸጥታ ኃይላት እየተዘዋወሩ ሲጠብቁም ተስተውሏል። የምዕመኑ ቁጥር ከአምናው እጅጉን ቀንሷል። በሶሪያ እና በሊቢያ የእርስ በእርስ ጦርነቱ እንዲያከትም ጥሪ ያስተላለፉት ርእሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ፤ በየመን፣ በኢራቅ፣ በሊቢያ እና ከሠሃራ በታች ባሉ ሃገራት እየተከሰተ ያለው በደል እና ግፍ እንዲያከትም ተማጽነዋል።

ወኪሎቻችን ከቫቲካን፣ ከብራስልስ እና ከዩናይትድ ስቴትስ ያጠናቀሩትን ዘገባ ልከውልናል። የበዓል አከባበሩ እሥራኤል ምን ይመስላል? ቃለ-መጠይቅ አድርገናል።

ዘገባዎቹን የድምጽ ማጫዎቻዎቹን በመጫን ይከታተሉ

ተኽለእዝጊ ገብረኢየሱስ

ናትናኤል ወልደሚካኤል

ገበያው ንጉሤ

ዜናነህ መኮንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ