የገና ገበያና የጀርመን ኤኮኖሚ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 16 2006ማስታወቂያ
እዚህ ጀርመን ደግሞ ለገና ያልወጣ ገንዘብ…… የሚል አባባል ባይኖርም ለበዓሉ ብዙ ገንዘብ ማውጣት የተለመደ ነው ። ለስጦታ ፣ ለድግስ ፣ ለአልባሳት ለቤት እቃ ና ለመዝናኛ ብዙ ገንዘብ ከሚፈስባቸው በዓላት ገና ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል ። ባለፈው ህዳርና በመገባደድ ላይ ባለው በታህሳስ ወር ብቻ ጀርመኖች ለገና ገበያ ያወጡት ገንዘብ ከ80 ቢሊዮን ዩሮ ይበልጣል ። ይህም የጀርመንን ኤኮኖሚ በማንቀሳቀስና በመታደግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዘግቧል ። ይልማ ከሰሞኑ በየገበያው ተዘዋውሮ የተመለከተውን እንዲሁም የዶቼቬለዎቹ Viktoria Klebe ና Madeleine Meier የዘገቡትን በዛሬው የኤኮኖሚው ዓለም ዝግጅት ያቀርብልናል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ