1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገዋኒ ወረዳ ግጭትና ነዋሪዎቹ

ዓርብ፣ ግንቦት 23 2005

ችግሩ ግን በልማዱ ፌደራል የሚባለዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት የሚቆጣጠረዉ ፖሊስ የሚፈፅመዉ-መስራት ካለበት መቃረኑ ወይም እንዲሰራ የሚገባዉን መስራት ባለበት ሥፍራ ሥፍራ አለመስራቱ እንጂ።

https://p.dw.com/p/18i2b
(FILE) A file photograph dated 2011 showing camels with their guide at Danakil desert in northern Ethiopia in front of Erta Ale volcano. Reports state that on 18 January 2012, the Ethiopian government said that two Germans, two Hungarians and an Austrian tourists were killed by gunmen as they visited Erta Ale volcano in the remote region of Afar in northern Ethiopia in early hours of 17 January. Gunmen also kidnapped two Germans and two Ethiopians while injuring a Hungarian and an Italian in an attack took place near the Eritrean border. Ethiopia blamed its neighbor Eritrea for the attack, but Eritrea dismissed the allegation. In 2007, five Europeans and 13 Ethiopians were kidnapped in Afar region that is prone to banditry and separatist rebel fighters' movement. EPA/JOSEF FRIEDHUBER
ምስል picture-alliance/dpa



በአፋር መስተዳድር በገዋኒ ወረዳ፥ ከገዋኒ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ገጠራማ መንደር ፖሊስ በያዝነዉ ሳምንት አጋማሽ ላይ በከፈተዉ ተኩስ ቁጥራቸዉ በዉል ያልተወቀ ሰዎች መቁሰላቸዉንና ከመኖሪያ ቀያቸዉ መፈናቀላቸዉን ነዋሪዎች አስታወቁ።የዓይን ምስክሮች እንዳሉት ፖሊስ በሰዎች ላይ ካደረሰዉ ጉዳት በተጨማሪ ተኩሱ ያስደነበራቸዉ ከብቶች ባዝነዉ ጠፍተዋል። ፖሊስ ከዚሕ ቀደም በወሰደዉ ተመሳሳይ እርምጃ ሰዎች መገደላቸዉም ተጠቅሷል።የወረዳዉ የፖሊስ መኮንን የተባሉ ግለሰብን በሥልክ ለማናገር ሞክረን ነበር።መልሳቸዉ ግራ አጋቢ ነዉ። ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።


ከዓይን ምስክሮቹ መሐል ገሚሶቹን በስልክ መስመር ጥራት ችግር ምክንያት ማነጋገር አልቻልንም። ጉዳቱ ደረሰብን የሚሉት ደግሞ አማርኛ አይችሉም።አስተርጓሚም አላገኙም።እሳቸዉ ግን ያዩ-የሰመቱን ነገሩን።


ሰበቡ ምስክሮቹ እንደሚሉት ሕገ-ወጥ የሚባል ጦር መሳሪያ ማስፈታት ነዉ።መሳሪያ እንዲፈቱ የሚገደዱት ወይም ሕገ-ወጥ የሚባሉት ደግሞ አንድም ከተማ ዉስጥ አለያም፥ ኢትዮጵያን ከኤርትራ፥ ወይም ከጅቡቲ በሚያገናኘዉ አስፋልት መንገድ ግራ ቀኝ የሠፈሩ ታጣቂዎች ናቸዉ።ትጥቅ የማስፈታቱ ዓለማ ዘረፋን ለመካለከልም ጭምር መሆኑን ነዋሪዎቹ ያምናሉ።

ችግሩ ግን በልማዱ ፌደራል የሚባለዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት የሚቆጣጠረዉ ፖሊስ የሚፈፅመዉ-መስራት ካለበት መቃረኑ ወይም እንዲሰራ የሚገባዉን መስራት ባለበት ሥፍራ ሥፍራ አለመስራቱ እንጂ።

ሥም-አድራሻቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉት ወይዘሮ እንደሚሉት ፖሊስ ሰዎችን ሲጎዳ ለገዋኔዎች የሰሞኑ አዲስ አይደለም።ከዚሕ በፊትም ፖሊስ እዚያ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ትጥቅ በማስፈታት ሰበብ ያንገላታል። ይደበድባል።ገድሎም ያዉቃል።


ሴትዮዋ እንደሚሉት ፖሊስ በነዋሪዎቹ ላይ ይፈፅማል የሚባለዉን በደል እንዲያቆም ነዋሪዎቹ ለአካባቢ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ አቤት ብለዉ ነበር።ግን በወይዘሮዋ አገላለፅ መፍትሔ የለም።ደግሞ ይጠይቃሉ።ማነን-እኛ አይነት-ጥያቄ።


የገዋኔ ወረዳ የፖሊስ ባልደረባ ናቸዉ ወደተባሉት ግለሰብ ሥልክ ደወልን።

ትንሽ አይደለም፥ ከብዙ ደቂቃ ምናልባትም ከአንድ ሠዓት የሥልክ ሙከራ በሕዋላ ሥልካቸዉን አነሱ።

ዘጉትም።

ARCHIV - Ein Mann vom Stamme der Afar ist mit einem Gewehr bewaffnet und beobachtet die Wüste um den Ort Hadar im Afar-Dreieck aus Sorge vor Übergriffen durch einen verfeindeten Clan (Archivoto vom 19.11.2005). Bei einem brutalen Überfall auf eine Reisegruppe in Äthiopien sind offenbar fünf Touristen getötet worden, darunter zwei Deutsche. Nach ersten Berichten geschah der Überfall auf die Reisegruppe in der Danakil-Wüste. Die Region ist einer der tiefsten Orte der Erde und wird vom Nomadenvolk der Afar bewohnt. Foto: Thomas Schulze dpa +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ