1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጊነዉ ፕሪዝደንት ሞትና ግልጽ ያልሆነዉ የአገሪቷ አስተዳደር

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 15 2001

በጊኒ የረጅም ግዜ ፕሪዝዳንት የሆኑት የላሳና ኮንቴን ህልፈተ ህይወት ከተሰማ በኻላ የአገሪቱ ወታደሮች የአስተዳደሩን መንግስት መቆጣተራቸዉን አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/GMVf
ጊኒን ለ24 አመታት የመሩት የ 74 አመቱ ፕሪዝደንት ላሳና ኮንቴንምስል picture-alliance/ dpa

የምዕራብ አፍሪቃዊቷን አገር ለ24 አመታት የመሩት የ 74 አመቱ ፕሪዝደንት ላሳና ኮንቴን ከትናንት በስትያ ምሽት ላይማረፋቸዉ ከተሰማ ከሰአታት በኻላ የአገሪቱ የጦር ሰራዊት አዛዦች የመንግስት ተቋማት በሙሉ መፍረሳቸዉን በመግለጽ የመንግስት ግልበጣን አካሂደዋል ይህንን ተከትሎም የአፍሪቃዉ ህብረት የሰላም እና ጸጥታዉ ምክር ቤት ዛሪ አዲስ አበባ ላይ የዝግ ዉይይት መያዙም ተገልጾአል። ላሳና ኮንቴን በልብ ህመም የስዃር እና በደም በሽታ ህመም ለብ’ዙ ግዜ መሰቃየታቸዉ ይነገራል። የላሳና ኮንቴን ከባድ አጫሽም ነበሩ።