1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጊኒ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 7 2003

በጊኒ ከዘጠኝ ቀናት በፊት በተካሄደው ሁለተኛው ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃውሞው ወገን መሪ አልፋ ኮንዴ አሸናፊ ሆኑ።

https://p.dw.com/p/QAWc
አሸናፊው አልፋ ኮንዴምስል AP

የጊኒ አስመራጭ ኮሚሽን ትናንት እንዳስታወቀው፡ ስድሳ ሰባት ከመቶ የመራጭ ተሳትፎ በነበረበት ምርጫ የሰባ ሁለት ዓመቱ ኮንዴ ሀምሳ ሁለት ነጥብ አምስት ከመቶ፡ ተፎካካሪያቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ሴሉ ዳሌን ዲያሎ አርባ ሰባት ነጥብ አራት ከመቶ የመራጭ ድምጽ አግኝተዋል። የምርጫውን ውጤት ላዕላዩ ፍርድ ቤት በይፋ ማጽደቅ ይኖርበታል። ተሸናፊው ዲያሎ ተጭበርብሮዋል ያሉት የምርጫ ውጤት ላይ አስፈላጊው ምርመራ ሳይደርግ በፊት ውጤቱን እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል።

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ