1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋምቤላው ግድያ ፣ ግጭት እና መፍትሄው

እሑድ፣ ሚያዝያ 23 2008

በጥቂት ቀናት ልዩነቶች ውስጥ የደረሱትን እነዚህን ጥቃቶች መንግሥት ፈጥኖ መከላከል አለመቻሉ ደግሞ እያስወቀሰው ነው ። ከግጭቱ በኋላም ስለተወሰዱ እርምጃዎች ግልፅ መረጃ ባለመስጠትም እየተተቸ ነው ።

https://p.dw.com/p/1IfY4
UNHCR Flüchtlingslage in Gambella Äthiopien
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የጋምቤላው ግድያ ግጭትና መፍትሄው

ከሁለት ሳምንት በፊት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ተሻግረው በጋምቤላ ክልል የፈፀሙት ግድያ ፣ እገታ እና ዘረፋ በሳምንቱ እዚያው ጋምቤላ በደቡብ ሱዳን ስደተኞችና በነዋሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉ ማነጋገሩ ቀጥሏል ። በጥቂት ቀናት ልዩነቶች ውስጥ የደረሱትን እነዚህን ጥቃቶች መንግሥት ፈጥኖ መከላከል አለመቻሉ ደግሞ እያስወቀሰው ነው ። ከግጭቱ በኋላም ስለተወሰዱ እርምጃዎች ግልፅ መረጃ ባለመስጠትም እየተተቸ ነው ።የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ትጥቅ እንዲፈቱ መደረጉ እንዲሁም የተጠናከረ የድንበር ጥበቃ አለመኖር ነዋሪዎችን ለጥቃት ያጋለጡ አበይት ምክንያቶች መሆናቸውን ተቃዋሚዎችና የመብት ተሟጋቾች ይናገራሉ ። የጋምቤላው ግድያ ግጭትና መፍትሄው ላይ ያተኮረውን ውይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ያዳምጡ ።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ