1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋምቤላ ግድያ የአድማጮች አስተየት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 13 2008

ከደቡብ ሱዳን የመጣ ለመሆኑ በተነገረለት የተደራጀ ታጣቂ ኃይል ለተገደሉት ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ የታወጀው የ2 ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን የሚያበቃው ዛሬ ነው። የተለያዩ አድማጮቻችን በፌስቡክ በአጭር መልእክት መቀበያ ስልካችን እንዲሁም በዋትስአፕ የላኩልንን አስተያየታቸውን አሰባስበናል።

https://p.dw.com/p/1IaU3
Karte Äthiopien Südsudan Gambella Englisch

[No title]

ዓርብ ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰዉ ጋምቤላ በገቡ የተደራጁ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ስለተገደሉ ኢትዮጵያውያን እና ስለታገቱ ሕጻናት ከአድማጮቻችን በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች አስተያየት ደርሶናል።

አስተያየታቸውን በአጭር መልእክት መቀበያ ስልካችን በጽሑፍ የላኩልን አድማጭ ነዋሪነታቸው በውጭ ሀገር ነው። በተፈጠረው ግድያ እጅግ እንዳዘኑ ገልጠውልናል። ከደቡብ ሱዳን ድንበር ጥሶ በጋምቤላ ጥቃት የፈጸመው የተደራጀ ኃይል የእኛን ደካማ ጎን በደንብ አውቆ እና አጥንቶ ነው ይላሉ።

አያይዘውም ጥቃቱ እንደሚደርስ እየታወቀ አስፈላጊው ቅድመ-ጥንቃቄ አለመደረጉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰዉ ጋምቤላ የገቡ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት የተገደሉት ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በዋትስአፕም መልእክቶች ደርሰውናል። ደውለን ያነጋገርናቸው አድማጭ ሐዘናቸውን ገልጠዋል።

Flash-Galerie Äthiopien Land Grab
ምስል DW/Schadomsky

በፌስ ቡክ ገጻችን ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል የተወሰኑትን እናቅርብላችሁ። አቡ ናጂኅ ዓሊ የተባሉ የፌስ ቡክ ተከታታያችን፦ «ትጥቃችሁን ፍቱ አላቸው መንግስት ትጥቃቸውን ፈቱ፤ ብዙ ሳይቆዮ ወገኖቻችን እሄ ችግር ደረሰባቸው ፍርዱን ለናንተ ። ድንቄም ከበባ።»

አዝመራው ብዙአየሁ በበኩላቸው፦ «ጀግነውና አይበገሬው ሰራዊት የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ነው፤ ነገር ግን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ እንደይካሄድ መንግስት አሁን በተጠቁ አካባቢዎች ሰራዊቱን ማስቀመጥ ይኖርበታል ብየ አምናለሁ» ብለዋል። አሥራት ማዴቦ ደግሞ፦ «ቅድመ ጥንቃቄ ባይደረግም የተወሰደዉ እርምጃ ጥሩ ነዉ። ግን ልጆቻችን መመለስ አለባቸዉ።» ሲሉ ዳዊት ባዩ በበኩላቸው፦ «የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን መጠበቅ አልቻለም! በጣም ያሳዝናል!!!» የሚል አስተያየት አስፍረዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ