1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኛ አማኑኤል በረከት ሥርዓተ-ቀብር፣

ማክሰኞ፣ ግንቦት 23 2003

በመጀመሪያ መምህር ነበረ፤ በኋላ የረጅም ዘመን የራዲዮ ጋዜጠኛ! ድሮ በብሥራተ ወንጌል ራዲዮ ጣቢያ ዓለምን እንይ! የሚል ተወዳጅ ዝግጅት ነበረው።

https://p.dw.com/p/RQxC
ምስል DW

በኢትዮጵያ ቴሌቭዥንም፣ ህዝብና ጤናው የተሰኘ ዝግጅት ያቀርብ ነበር። በዶቸ ቨለ ይበልጥ የሚታወቀው በእስፖርት ፕሮግራም አዘጋጅነቱ ነው። ከ 4 ዓመት ከመፈንቅ ገደማ በፊት ጡረታ እስከወጣበት ጊዜ ድረስም በተጨማሪ የአማርኛው ክፍል ኀላፊ ነበረ። አማኑኤል በረከት ሥራውን እጅግ የሚወድ፤ በሥርዓት የታነፀ፣ ከሰዎች ጋር በጣም ጥሩ የመግባባት ችሎታ የነበረው፤ በመቻቻል የሚያምን፣ ሰዎችን ለማስደሰት የሚንሠፈሰፍ፤ እጅግ ሰላማዊ፤ ትሁትና ለጋስ ሰው ነበረ።

በዛሬው ዕለት ቦን አቅራቢያ በምትገኘው «ባድ ሆኔፍ» በተባለችው ከተማ፤ ከዩናይትድ እስቴትስ የመጡት እህቱ፤ ወንድሞቹ፤ በጀርመን የሚገኙት ባለቤቱ፤ ልጁ፣ የልጅ ልጆችና ቤተሰብ፣ ዘመዶች፣ እንዲሁም ከቦን ኮሎኝና ከሌሎችም የጀርመን ከተሞች ፣ በዛ ያሉ የረጅም ጊዜ ወዳጆቹ፣ ጓደኞቹና የሥራ ባልደረቦቹ በተገኙበት የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል። ከDW የአማርኛው ክፍል ሌላ፤ የተለያየ ቋንቋ ክፍል ሠራተኞችም የተገኙ ሲሆን፤ የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት ለሥርጭታችን በሚያመች መልኩ መሳይ መኮንን ተከታትሎታል።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ