1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኞች ጥያቄና የጠ/ሚ ዐቢይ መልስ  

ዓርብ፣ መጋቢት 20 2011

አዲስ አበባ ለዘመናት ከፍቶት የመጣን ኢትዮጵያዊ ሁሉ እጇን ዘርግታ ትቀበል ነበር፤ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የጎረቤት ሀገር ዜጎችንም እንደዛው ስትቀበል የነበረች ናት፡፡ ሁሉንም አቅፋ የምትኖር ከተማም ናት፡፡ ስለዚህ እቺ ከተማ የእከሌ የእከሌ ሳትሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት፡፡

https://p.dw.com/p/3Fu0f
Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

የጋዜጠኞች ጥያቄና የጠ/ሚዉ መልስ    
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አዲስ አበባን በሚመለከት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተለያዩ ብዙኃን መገናኛ ጋዜጠኞች ለቀረበላቸዉ ጥያቄዎች ከሰጡት መልስ ዉስጥ አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ሃብት መሆኗን ተናግረዋል። "አዲስ አበባ የሁላችንም ናት፡፡… አዲስ አበባ ለዘመናት ከፍቶት የመጣን ኢትዮጵያዊ ሁሉ እጇን ዘርግታ ትቀበል ነበር፤ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የጎረቤት ሀገር ዜጎችንም እንደዛው ስትቀበል የነበረች ናት፡፡ ሁሉንም አቅፋ የምትኖር ከተማም ናት፡፡ ስለዚህ እቺ ከተማ የእከሌ የእከሌ ሳትሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት፡፡" ሲሉ ተናግረዋል። በጋዜጣዊ መግለጫዉ ላይ የነበረዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዩሃንስ ገብረግዚአብሔር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።  

ዩሃንስ ገብረግዚአብሔር


አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ