1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመኪና አደጋ 13 ሞቱ 10 ቆሰሉ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 22 2009

ወደ ሥራ ቦታቸው በማምራት ላይ የነበሩ የግልገል ጊቤ ሁለት የኃይል ማመንጫ ሰራተኞችን የጫነ ተሽከርካሪ ተገልብጦ 13 ሰዎች ሲሞቱ 10 ሰዎች ቆሰሉ።

https://p.dw.com/p/2hMJp
Äthiopien Omo Fluss Tal Landschaft
ምስል JENNY VAUGHAN/AFP/GettyImages

የሰራተኞች ማጓጓዣው 23 ሰዎችን ጭኖ ነበር። የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የኮምዩንኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አስቴር ተክሌ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። «  ከትራፊክ አደጋ ነው እኛም መረጃው የደረሰን። መኪናው ተገልብጦ ይመስለኛል። የተጣራ ነገር የለም። የሰራተኞች ሰርቪስ ነበር። ሰራተኞች ሞተዋል። ወደ ስራ ሲሄዱ የነበሩ ናቸው። »
ከሰባት ዓመት በፊት የተመረቀው የግልገል ጊቤ ሁለት የኃይል ማመንጫ በኦሮሚያ ክልል ከጅማ 80 ኪሜ በስተ ምስራቅ ርቀት ላይ ይገኛል። የኃይል ምንጩ የኦሞ ወንዝ ነው።

ልደት አበበ

እሸቴ በቀለ