1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግል መዋዕለ-ነዋይና የኢትዮጵያ ልማት

ረቡዕ፣ ሰኔ 13 2004

የጀርመንን የግል ኤኮኖሚ ዘርፍ መዋዕለ-ነዋይ ወደ ኢትዮጵያ በመሳብ ላይ ያለመ አንድ የጀርመንና የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ጉባዔ በቅርቡ ኮሎኝ ከተማ ውስጥ ተካሂዶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

https://p.dw.com/p/15Hwh
ምስል DW

የጀርመንን የግል ኤኮኖሚ ዘርፍ መዋዕለ-ነዋይ ወደ ኢትዮጵያ በመሳብ ላይ ያለመ አንድ የጀርመንና የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ጉባዔ በቅርቡ ኮሎኝ ከተማ ውስጥ ተካሂዶ እንደነበር የሚታወስ ነው። በጉባዔው ላይ የጀርመን ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ-ነዋይ እንዲያደርጉ ለመሳብ ከተወሰነ የታክስ ነጻነት ጀምሮ እስከ ርካሽ የሥራ ጉልበት ብዙ ማራኪ የሚሆን ምክንያት ተዘርዝሯል።

እርግጥ ስብሰባው ለጀርመን ኩባንያዎች የተወጠነ ቢሆንም በውጭ የሚኖሩ መዋዕለ-ነዋይ ለማድረግ አቅም ያላቸው ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ግን ጨርሶ አልተነሣም። ስለ ጉባዔው ሂደት ባለፈው ሣምንት አጠቃላይ ዘገባ ማቅረባችን ሲታወስ ዛሬ የምናሰማችሁ ደግሞ በጉዳዩ ከኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኤጀንሲይ የምርምርና የማራመጃ ዘርፍ ሃላፊ ከአቶ አክሊሉ ወ/ማርያም ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ነው።

ለአቶ አክሊሉ ወ/ማርያም በመጀመሪያ ያነሳነው ጥያቄም ኢትዮጵያውያን የመዋይለ-ነዋይ ባለቤቶችን ለመሳብብ ምን እየተደረገ እንደሆነና በአጠቃላይ የግሉ መዋዕለ-ነዋይ ይዞታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እንዲገልጹልን ነበር።

መሥፍን መኮንን

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ